የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለአቬሽን ደህንነት ዋና መምሪያ ሰራተኞች የሚሆን የቆዳ ቀበቶ አምራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለአቬሽን ደህንነት ዋና መምሪያ ሰራተኞች የሚሆን የቆዳ ቀበቶ አምራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 17, 2026)

የቆዳ ቀበቶ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SSNT-T636

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለአቬሽን ደህንነት ዋና መምሪያ ሰራተኞች የሚሆን የቆዳ ቀበቶ አምራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል::

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አምራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡

1. ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች እና በሙያ ዘርፉ ሶስት (3) ዓመት እና ከዚያ በላይ የሰሩ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T636 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ሃያ አምስት ሺህ ብር (25,000.00) በባንክ በተረጋገጠ .. (CPO) ወይም 120 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቛም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ተጫራቾችን የጨረታ ማስከበሪያ ለተጨማሪ ቀን የሚቆይበት ጊዜ እንዲራዘምለት የመጠየቅ መብት አለው።

4. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ሰኞ, ነሐሴ 25 2018 . እስከ ጠዋት 1030 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ጠዋት 5:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ:-

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517-8025

ሜይል: WoldeM@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *