ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Reporter (Aug 19, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የእውቅና ፈቃድ አግኝቶ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጀሞ አካባቢ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት ላይ የሚገኝ የትምህርት ተቋም ነው::

በመሆኑም የደንብ ልብስ ከታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ከአቅራቢ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

ጨረታው ላይ የምትሳተፉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ጀሞ 1 ለቡ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ድርጅታችን ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር C116 በአካል መጥታችሁ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን አናሳውቃለን::

አጫራቹ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 0974-17-66-00 / 0974-17-66-17 መደወል ትችላላችሁ::

1. በድጋሚ የወጣ የደንብ ልብስ

ለግዥ የተፈለገው የተለያዩ ደንብ ልብስ መስፈርቶች

.

ዓይነት

ብዛት

መግለጫ

1

የጥበቃ ሙሉ የደንብ ልብስ ሎጎ ያለው ከነኮፍያው

29

እርሳስ ቀለም

2

የጥበቃ ጃኬት

29

አረንጓዴ ቀለም

3

የጥበቃ ካፖርት

29

ጥቁር ሰማያዊ ቀለም

4

የጥበቃ የዝናብ ልብስ

29

ጥቁር ሰማያዊ ቀለም

5

የፅዳት ሙሉ የደንብ ልብስ ሎጎ ያለው ሱሪ እና አላባሽ

16

ውሃ ሰማያዊ ቀለም

6

ጋዎን ሎጎ ያለው

4

እርሳስ ቀለም

7

የሹፌር ጋዎን ሎጎ ያለው

2

ጥቁር ሰማያዊ ቀለም

8

የነርስ ጋዎን ሎጎ ያለው

2

ነጭ ቀለም

9

የሜንቴናንስ ሙሉ ልብስ

3

እርሳስ ቀለም

10

ተላላፊ ቁልፍ ያለው የሼፍ ልብስ ከነኮፍያው ሎጎ ያለው

4

ነጭ ቀለም

11

የካፍቴሪያ ሽርጥ ከነኮፍያው ሎጎ ያለው

4

ጥቁር ሰማያዊ ቀለም

12

የአትክልተኛ ሙሉ ቱታ ሎጎ ያለው

3

ጥቁር ሰማያዊ ቀለም

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *