Addis Zemen (Aug 19, 2026)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር GGWW/0001/2019
በማዕከላዊ ኢትዮዽያ ከልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በ RDF በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኝ ለግብርና ሴክተር የሚሆን የRDF መድኃኒትና ዕቃዎችን በጫረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ለግዢ የቀረቡ እቃዎችና የጫረታ ማስከበሪያ CPO
- ሎት አንድ ፡ የRDF መድኃኒትና ዕቃዎች ፡ የጫረታ ማስከበሪያ 10000 ብር
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች ፡–
1. የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት ና የቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት በኦላይን /online/ ሲስተም የተመዘገበ መሆን አለበት።
3. በጫረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጫረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው።
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ ቀናት 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100 ብር/አንድ መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ የጨረታው ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጫረታውን ቴክኒካል ና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ፡ ሀ/ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት እና ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል ና ሁለት ፎቶ ኮፒውን ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ የተጠቀሱት የጫረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ፋይናንሻል ዶከመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስረኛው/ ተከታታይ ቀናት ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት ለጫረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም መሰራት አለበት።
7. የጫረታው ሰነድ በ10ኛው ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ከቀኑ 8፡30 ደግሞ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ ፡–
1. በግዢ ኤጀንሲ በመድሀኒት አቅርቦት ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶችም መወዳደር አይችሉም
2. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉዋቸው የመድሀኒት የጥራትችግር ያለባቸው መሆናቸው በቴክኒክ ጥራት ኮሚቴ ከተረጋገጠ ተመላሽ መሆኑን።
3. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉዋቸው ማንኛውም መድሀኒት የወረዳው ማዕከል ማለትም ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መሀል አምባ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የወረዳው ማእከል ርቀት ከአዲስ አበባ 116ኪ.ሜ ነው።
4. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜ ና እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
ለበለጠ መረጃ፡– 0113 360 631 / 0113 360 146
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት