Addis Zemen (Aug 19, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01
በአርሲ ዞን የሲርካ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ የፅዳት ዕቃዎች፤ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤ የመኪና ጎማ፣ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸሮች)፤ ትናንሽ ቋሚ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
1. ለተጠየቁት የግዢ ዕቃዎች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱና በፌዴራል ወይም በክልል ገንዘብ ጽ/ቤት በአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡበትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው እንዲሁም፤ የግብር ከፉይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ለሠራተኞች የደንብ ልብስ፤ ለጽዳት ዕቃዎች፣ ለጽሕፈት መሣሪያዎች፤ ትናንሽ ቋሚ ዕቃዎች፤ የመኪና ጎማ እና የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸሮች) ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) በሲርካ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎቤሳ ቅርንጫፍ በባንክ ኔትዎርክ በሂሳብ ቁጥር 1000065220133 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ የጽ/ቤቱ የግዢና የንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ ብሩን ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ስሊፕ አድቫይስ ይዞ በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በተለያየ ፖስታ በኦርጅናልና በኮፒ በማዘጋጀት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት በመሙላት ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት ማቅረብ አለባቸው።
6. የተጫራቾች ሙሉ ስም፤ ፊርማ፤ የድርጅቱ ማህተምና አድራሻ የሌለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
7. የጥቃቅንና አነስተኛ ማይክሮ ኢንተርፕራይዞች ለዚህ የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ እንደዋስትና የሚያገለግል ከጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ሥራዎች ጽ/ቤት ብቻ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይችላሉ።
8. አሸናፊው ተጫራች የዕቃዎቹ ናሙና ቀርቦ እንዲታይ ከተፈለጋ የተፈለጋውን ዕቃ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
9. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዋጋ ከዚህ ሰነድ ውጪ በሌላ ዋጋ መስጫ ላይ ሞልተው መመለስ አይችሉም።
10. ተጫራቾች የሀገሪቱን የፌዴራልና የክልሉን የግዥ አዋጆች፤ ደንቦችንና መመሪያዎችን የማክበርና ከማንኛውም የሙስና ድርጊቶች ነጻ የሆኑ እንዲሁም፤ በዕቃ አቅርቦት ወቅት ከዚህ ሰነድ ጋር የተያያዘውን የውል ሰነድ መፈረም ይኖርባቸዋል።
11. አሸናፊ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሰጡት ነጠላ ዋጋ እስከ ጥር 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን አውቀው ጽ/ቤቱ ተጨማሪ የግዢ ጥያቄ ፍላጎት ባቀረበበት ወቅት ለማቅረብ ፍላጎት ያላቸውና ውል መፈፀም የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
12. አሸናፊ ተጫራች ጽ/ቤቱ ከሚያደርገው የግዢ ውል 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት የሚችል መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል።
13. ተጫራቾች የሠራተኞች የደንብ ልብስ ዓይነቶችን (ብትን ጨርቅ፤ የተዘጋጀ ልብስና ጫማዎችን) ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
14. ማንኛውም ተጫራች ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ለሠራተኞች የደንብ ልብስ ፤ የመኪና ጎማዎች እና ለቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸሮች) ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. (C.PO.) ብቻ በሲርካ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በማሠራት ማቅረብ ይኖርበታል። ለጽዳት ዕቃዎች፤ ትናንሽ ቋሚ ዕቃዎች እና ለጽሕፈት መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ብር 10,000 (አስር ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. (C.PO.) ብቻ በሲርካ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በማሠራት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች ሲ.ፒ.ኦ. (CPO)ውን ለብቻ በታሸገ ፖስት ማቅረብ አለባቸው።
15. አሸናፊ ተጫራች ለውል ማስከበሪያ ያስያዘው የገንዘብ መጠን እስከ ሦስት ወር የጊዜ ገደብ ድረስ ገቢ ያደረጋቸው ዕቃዎች ለተጠቃሚው መ/ቤት ደርሰው የብቃት ደረጃቸው ትክክለኛነት እስኪረጋገጥ ድረስ የማይመለስ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል።
16. ተጫራቾች በማንኛውም ሁኔታ የጨረታውን አካሄድ ሥነ-ሥርዓት ለማስቀየርም ሆነ ለማሳሳት ከሞከሩ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ተደርጎ ወደፊት በሚወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ላይ እንዳይሳተፉ ይደረጋል።
17. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው የዕቃ ዋጋዎች (የመወዳደሪያ ሃሳቦች) የተጨማሪ እሴት ታክስ ማካተቱንና አለማካተቱን በግልጽ መግለጽ ይኖርባቸዋል:: ይህ ያልተገለጸ ከሆነ፣ የተሰጠው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዳካተተ ይወሰዳል።
18. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና ዕቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ የታዘዘውን ዕቃ በአንድ ላይ ሲርካ ወረዳ ጎቤሳ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
19. ጽ/ቤቱ ተጫራቾችን ሲያጫርት ለጨረታው ቅድመ ግምገማ ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን የተጫራቾች መመሪያ መሠረት በማድረግ ለቀረቡት የዕቃ የቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ የዕቃዎቹን ጥራትና ብቃት በማረጋገጥ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ድርጅት አሸናፊ ይሆናል።
20. በጨረታው ማስታወቂያ ውስጥ ያልተገለጹ መመሪያዎች ካሉ ስራ ላይ ባሉት የመንግስት የግዥ አዋጆች፤ ደንቦችና መመሪያዎች መሰረት የሚፈጸሙ ይሆናሉ።
21. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት በ5፡00 ሰዓት ጽ/ቤቱ ውስጥ ለአመቺነቱ በተመረጠው ቦታ ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
22. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአርሲ ዞን የሲርካ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት