በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በስሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎችን፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በስሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎችን፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 19, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ /ቤት 2019 በጀት ዓመት በስሩ ላሉት ሴክተር /ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ፤ የጽዳት እቃዎችን፤ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፤ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡

1. በዚህ ዘርፍ የንግድ ፍቃድ ያለው 2018/2019 የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

2. አሸናፊው ድርጅት ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በአስር ቀን ውስጥ ያሸነፋቸውን እቃዎች ገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ /ቤት ማቅረብ የሚችል።

3. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የያዘ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ 16ኛው ቀን በስራ ሰዓት እስከ 630 ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በሲንቄ ባንክ 1055210501213 በመክፈል የባንክ ስሊፕ በማምጣትና ከገቢዎች በማወራረድ ከገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ /ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች እያንዳንዱን እቃ የሚሸጡበትን ዋጋ የያዘ ዝርዝር የዋጋ ሰነድ በፖስታ በማሸግ ጋዜጣ ከወጣት 16ኛው ቀን እስከ 8:00 ሰዓት ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000/ ሰላሳ ሺህ ብር/ ወይም ሲፒኦ በማስያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ያስገባሉ።

5. ጨረታው 16ኛው ቀን 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ /ቤት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።

6. በሌላ ሰው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

7. ተጫራቾች ለሙያቸው ማረጋገጫ የስራ ልምድ እና የምስጋና ደብዳቤ ቢያቀርቡ ይመረጣል።

8. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 20 76 27 50 / 09 10 28 50 05 / 09 22 83 14 58 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ /ቤት