Addis Zemen (Aug 19, 2026)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት የኢቨንት ኦርጋናይዘር አገልግሎት፣ የሰራተኞች ካፌና የመኪና ኪራይ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ ኦንላይን የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000-70-96-80-882 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን አካውንት ላይ አስገብታችሁ ደረሰኙን ይዛችሁ በመምጣት ሰነዱን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 706 ማግኘት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ከዚህ በታች በሰንጠረዡ በተገለፀው የዕቃዎች ምድብ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
|
ሎት ቁጥር |
የዕቃ ምድብ |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና |
|
ሎት 1 |
የኢቨንት ኦርጋናይዘር አገልግሎት |
100,000 |
|
ሎት 2 |
የሰራተኞች ካፌ አገልግሎት |
20,000 |
|
ሎት 3 |
የመኪና ኪራይ |
20,000 |
4. ተጫራቾች የመወዳዳሪያ ሀሳባቸውን ዋናውንና ኮፒውን በየሎቱ በመከፋፈል /ቴክኒካል ኦሪጅናል ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
5. በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
6. በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ከመ/ቤታችን ጋር ጨረታውን እንዳሸነፈ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ በሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል።
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በሚገኙበት ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት 7ኛ ፎቅ በሚገኘው በኮሚሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
8. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡–
አራዳ ክ/ከተማ፡– አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ጎን፣ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ህንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር፡-251-011-125-0733
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን