2merkato.com (Aug 19, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
“SHEHID Trading” ከታች በሰንጠረዥ የተገለጹትን የተለያዩ ለድርጅቱ ስራ አገልግሎት የሚዉሉ ዕቃዎችን በየሎታችው በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት የእቃዎች መግለጫ
- የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች
- የተለያዩ ንጽህና ዕቃዎች
- የታሸገ ውሃ አቅርቦት
- የኤልክትሮኒክስ እቃዎች
- የቢሮ ዕቃዎች (furniture)
በመሆኑም ተጫራቾች-
1. ተጫራቾች በየሎቱ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺ) ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በድርጀቱ የቴሌብር አካውንት 0942186677 (ZEDEN) ገቢ በማድረግ፣ ገቢ ያደረጉበትን ደረስኝ ፎቶ በድርጀቱ የቴሌግራም አካዉንት ስልክ ቁጥር 0942186677 በመላከ፣ ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾችን መመሪያ እና የዕቃዎችን ዓይነትና መጠን የያዘ ሶፍት ኮፒ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላላሉ፡፡
2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ተጫራቹ የዕቃው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚሸጡበትን የነጠላ ዋጋ በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው፤ በታሸገ ኤንቨሎፕ የኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
3. ተጫራቾች በጨረታ ሰንድ ላይ በተጠቀሰው መሰረት የቴክኒካል እና ፋይናንሻል የጨረታስ ሰንድ አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ ማስገባት አለባቸው፡፡
4. ትክክለኛ የተጫራች ስምና አድራሻ በታሽገ ኤንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሰነድ ላይ መግለፅ ይገባል፣
5. ተጫራቾች የእቃዎችን ለተቀመጠው የነጠላ ዋጋ ድምር የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ቢሮ ልደታ አህመድ የገበያ ማዕከል ፣ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 334 ይከፈታል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታውን ውጤት በድርጅቱ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥራችን 0942186677 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ ስምና ፊርማ ማስገባት አለባቸው
10. ተጫራቾች የቫት ሠርተፍኬት የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ ሠርተፍኬት እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11. ድርጅታችን የተሻል መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
SHEHID Trading
አድራሻችን ልደታ አህመድ የገበያ ማዕከል ፣ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 334