Be'kur (Aug 17, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል የፅህፈት፤ የፅዳት እቃ እና ህትመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም
1. ተጫራቾች እቃዎችን ወይም አገልግሎቾችን ለማቅረብ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያወጡ፣ የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ አመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን ካርድ) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
4. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጪዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ከገንዘብ ያዥ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማረኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
8. በዚህ ጨረታ መጫረት የምትፈልጉ በማያሻማ ሁኔታ በመሙላት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
10. አንድ ተጫራች ባወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ቢያስፈልግ ጨረታውን ላወጣው መስሪያ ቤት በፅሁፍ ወይም በስልክ ቁጥር 058 661 0330 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡ ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤትም የተጠየቀውን ጥያቄ ማብራሪያ የሚያሰጥ ሆኖ ሲገኝ ለሁሉም ተጫራቾች በጽሁፍ ወይም በፋክስ ጨረታው ከመከፈቱ ከ5 ቀናት በፊት መልስ ይሰጣል፡፡
11. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
13. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እሁድ፣ ቅዳሜና በዝግ ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተጠየቀው ስዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
14. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች አሸናፊው ከተለየ በኋላ የሚመለስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 (አምስት ሽህ ብር) ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል