በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተሮች መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተሽከርካሪ ጎማ ከነ ካላማዳሪው እና ለቪዲኦ እና ለፎቶ ማንሻ አገልግሎት የሚውል ካሜራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተሮች መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተሽከርካሪ ጎማ ከነ ካላማዳሪው እና ለቪዲኦ እና ለፎቶ ማንሻ አገልግሎት የሚውል ካሜራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Aug 17, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተሮች መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተሽከርካሪ ጎማ ከነ ካላማዳሪው እና ለቪዲኦ እና ለፎቶ ማንሻ አገልግሎት የሚውል ካሜራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡

1. ተጫራቾች በስራ ዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

3. የግብር ከፋይ (ቲንነምበር) ያላቸው።

4.  የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉንማስረጃዎች ፎቶ ኮፒከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ።

6. የጨረታ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሠነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 10 ማግኘት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት እቃ ዋጋ 10,000(አስር ሽህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረት የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።

9. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ በማሸግ አየሁ/ጓ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 08 ስምና አድራሻ በመፃፍ የጨረታ ፖስታዉን አሽገዉ በጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ወይም ለግዥ ኦፊሰር ወይም ለቡድን መሪ ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

10. ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ በስራ ሰዓት ሠነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በ3፡30 ይዘጋና በ4፡00 ይከፈታል።

11. የዋጋ መሙያው ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ የሌለዉ መሆን ይኖርበታል።

12. የጨረታዉ አሸናፊ ድርጅት የሚለየዉ በሎት ይሆናል።

13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. የጨረታው አሸናፊ እቃ አግልግሎት እስከ አየ/ጓ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።

15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አየሁ ጓ/ወ/ገ/ኢ/ት/ግዥና ንብረት አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 08 በአካል በመገኘት፣ በስልክ ቁጥር 058 387 8095 ወይም በሞባይል ቁጥር 09 18 78 03 22 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

የአየሁ ጓጉሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *