በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የወረታ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በጤና ጣቢያው በ2019 ዓ/ም የበጀት ዘመን ጀኔሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የወረታ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በጤና ጣቢያው በ2019 ዓ/ም የበጀት ዘመን ጀኔሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Aug 17, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የወረታ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በጤና ጣቢያው በ2019 ዓ/ም የበጀት ዘመን ጀኔሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የእቃው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ወይም (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምሰክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ21 ቀን የሚቆይ ሲሆን በ21ኛው ቀን በ6፡00 ተዘግቶ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በወረታ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 02 ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ወረታ ከተማ አስተዳደር ጤ/አጠ/ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 02 መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደርበት የእቃ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በጥንቃቄ ሞልቶ ኮፒና ኦርጅናል ሰነዱን በተለያየ ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን አድራሻ ህጋዊ ማህተም እና ስም ፊርማ በመጻፍ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቡድን መሪ ወይም ቢሮ ቁጥር 02 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ21 ቀናት የሚቆይ ሆኖ ዘወትር በሥራ ስዓት ፖስታውን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. እቃውን በተጠየቀውና በተሞላው (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ወረታ ጤና ጣቢያ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  11. ፖስታው ላይ ህጋዊ ማህተምና ሰነዱ ውስጥ ስም፣ ልዩ ፊርማና ማህተም መኖር አለበት፡፡
  12. ለጀኔሬተሩ ሁለት አመት ዋሰትና ውል መያዝ አለበት፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. የሚቀርቡ እቃዎች በሳምፕሉ መሰረት ሲሆን ዝርዝር መግለጫው (ሰፔሲፊኬሽን) ጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ማግኘት ይቻላል፡፡
  15. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 446 00 67 /058 446 06 49 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ጥሬ ገንዘብ ፖስታው ውስጥ ማስገባት አይቻልም፡፡
የወረታ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *