Addis Zemen (Aug 20, 2026)
የግንባታ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የአንድ ፑል ማዕከል ተጠቃሚ በሆነው በጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ የበጀት ድጋፍ በራጴ ወረዳ ብርዳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ግንባታ ቀሪ ሥራ ለማስገንባት በዘርፉ በደረጃ GC/BC 5 እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፤
ስለዚህ በመስኩ የተሠማራችሁ ተጫራቾች፣
- ደረጃቸው GC/BC 5 እና ከዚያ በላይ የሆነ፤
- የዘመኑን ግብር የከፈለና የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያለውና ማቅረብ የሚችል፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- በከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር የተመዘገቡና የታ እና ቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የተመዘገበና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የ2018 በጀት ዓመት ከግብር ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ከገቢዎች የተሰጠ ሰርተፍኬት የሚያቀርብ፤
- በክልሉ እና በዞናችን ውስጥ በግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው ሥራዎችን ያላስተጓጎሉ ውል ያላቋረጡ መሆን ይገባቸዋል፤
- የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይረክቶሬት ዘውትር በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመውሰድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ የጨረታ ሰነድ እያንዳንዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ አንድ ላይ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት በ22ኛው ቀን ይሆናል።
- ኦርጅናል ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ በሚታይ መልኩ በድጋሚ መጻፍ አለበት፤
- በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የተቋራጩ ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፤
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ለ21 ተከታታይ ቀን ከዋለበት በኃላ በ22ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ለ90 (60+30) ቀን የሚቆይ በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ እና በኢንሹራንስ ዋስትና መቅረብ አይቻልም፤
- ጨረታዉ የሚገመገመዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት እንደገና ተሻሽሎ በወጣው የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 70/2017 እና በዚሁ መመሪያ ላይ ማብራሪያና ማሻሻያ በተደረገው መሠረት ነዉ።
- በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውድድር ዉጭ ይደርጋል፤
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046130108 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት