Be'kur (Aug 17, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን በወረዳው ለሚገኝ ሴ/መስሪያ ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች እና እስቴሽነሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ለይቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚፈለገውን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (በመሂ 1) የተቆረጠ ጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ኮፒ አድርገው በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ከነሐሴ 11/2018 እስከ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም 12፡00 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ነሐሴ 26/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸውንና ፊርማቸው የድርጅቱ ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስ/ቡድን በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 271 02 69/058 271 00 31 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት