Addis Zemen (Aug 21, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢት/ያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. ሎት-1. ጽ/መሳሪያ ሎት-2. ህንጻ መሳሪያ ሎት 3 ኤልክትሮኒክስ ሎት-4 የተለያዩ ህትመቶች ሎት-5. የግንባታ ግብዓቶች ሎት-6. ሻይ ቡና መሰተንግዶ ሲሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉት፡–
2. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉት በሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገቡና ለ2019 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በ EGP የተመዘገቡ፣ ከዚህ በፊት ላከናወናቸው ተመሳሳይ ሥራዎች አገልግሎቶች ከአሠሪው አካል የመልካም ሥራ አፈጸጻም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) ከታች ከተጠቀሰው አድራሻ መግዛት ይችላሉ።
4. የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በማቅረብ መግዛት ይችላሉ።የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሂደት ቢሮ ይገኛል።
5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 (አራት ሰዓት) ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ። ዘገይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል።
6. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል። 16ኛው ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ለእያንዳንዱ፡– ሎት-1 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሎት-2 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሎት 3 ኤልክትሮኒክስ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሎት-4 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) ሎት-5 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) ሎት-6 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. ርክብክብ የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳዳር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይሆናል።
9. የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 046 180 0863 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ