የሀላባ ዞን ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል የመድኃኒት እና የህክምና እቃዎችን በግልፅ ጫረታ ማስታወቂያ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸዉ ድርጅቶች እና ነጋዴዎችን አወደድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሀላባ ዞን ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል የመድኃኒት እና የህክምና እቃዎችን በግልፅ ጫረታ ማስታወቂያ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸዉ ድርጅቶች እና ነጋዴዎችን አወደድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 21, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ – መ/ቁ01 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሀላባ ዞን ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት በጨረታ መለያ ቁጥር ሀ/አጠ/ሆ ዐl/2018 ለሆስፒታሉ ለሥራ አገልግሎት የሚዉሉ የመድኃኒት እና የህክምና እቃዎችን በግልፅ ጫረታ ማስታወቂያ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸዉ ድርጅቶች እና ነጋዴዎችን አወደድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

በጨረታዉ መሳታፍ የሚፈልጉ ተጫረቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸዉ::

  1.  ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ኦርጅናል እና ኮፒየመንግስት አገልግሎት ግዥ በአቅራቢነት ለመሳተፍ የሚያስችል የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ኦሪጅናልና ኮፒ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ክፍያ ምስክር ወረቀት/TIN number/ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ካሽጉ በኋላ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  2. እያንዳንዳቸው ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000/አስር ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ /RV/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ::
  3.  ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገፅ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም በማኖር ዋናውን ሰነድ በአግባቡ በታሸገ ኢንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በግልፅ ኢንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ታክስን (VAT) የሚያካትት መሆን አለበት:: ካልሆነ እንደተካተተ ተደርጎ ይወስዳል::
  4. የጨረታ ዶክመንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በመደበኛ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 57 በአካል በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ በስራ ሰዓት ቀርበዉ መዉሰድ ይችላሉ::
  5. የጨረታዉ ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጠበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ ቀን ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕገዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳጥኑ ይከፈታል:: ነገር ግን 16ኛዉ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታዉ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ህጋዊወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል::
  6. አሸናፊ የሆነ አቅራቢ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃዎችን የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ እንድሁም የትራንስፖርት በራሱ ወጪ የሚያቀርብ ይሆናል::
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነዉ::

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0465560281/0926182111/0941985165 ላይ መደወል ይቻላል::

አድራሻ፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሀላባ ዞን

የሀላባ ዞን ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *