Addis Zemen (Aug 22, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-001/2019
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ስር ለሚገኙ ለባለበጀት መስሪያ ቤቶች መጠቀሚያ ዕቃዎች፣ጫጩት እና የአትክልት ዘር:
- ሎት 1፡-የደንብ ልብስ
- ሎት 2፡-የፅህፈት መሳሪያ
- ሎት 3:የህትመት ውጤቶች
- ሎት 4: የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 5፦ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
- ሎት 6:የመኪና ጎማ እና የወንበር ልብስ
- ሎት 7:-መስተንግዶ ምግብ፣የታሸገ ውሀ፣ ለስላሳ መጠጦች፣የታሸጉ ምግቦች እና ኬክ/
- ሎት 8፡-የህዝብ ማመላለሻ መኪና ኪራይ /እስከ 26 ሰው የሚጭን
- ሎት 9፡-ዶሮ እንቁላል ጣይ እና የአትክልት ዘር
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የጨረታው መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
1 ለሎት 1፡30,000 ብር፣ለሎት 2፡-25,000 ብር፣ለሎት 3፡16,000፣ለሎት 4፡20,000፣ለሎት 5፡-5,000፣ለሎት 6፡- 10,000፣ለሎት 7፡7,000፣ለሎት 8፡6,000 እና ለሎት 9፡15,000 በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፡የቫት እና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቶች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 በመክፈል ከል/ክ/ከ/ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው እቃዎች በእያንዳንዱ ነጠላ ዋጋ ላይ ቫት ጨምረው መሙላት ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታው አሸናፊ ውል ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ እቃውን በራሱ ትራንስፖርት በሰጠው ናሙና መሰረት ንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርበታል።
7. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት በተወዳደሩባቸው ሎቶች ላይ ከሎት 6 ከመኪና ኪራይ ውጪ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል
9. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5/አምስት/ ቀን ውስጥ የውል ስምምነት ማስከበሪያ ባሸነፈበት ጠቅላላ ብር ላይ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርበታል።
10. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን ንብረት ውል በገባ በ15 ቀን ውስጥ ማቅረብ ይኖርበታል።
11. በአንድ ዕቃ ላይ ሁለት የተለያየ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታው ያሰርዛል።
12. ተጫራቾች በምዝገባ ፈቃድ ጀርባ የሚገኘው የስራ መስክ ኮፒ አድርጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
13. የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በአስራ አንደኛው(11ኛው) ቀን በ4፡00 ሰአት ታሽጎ በእለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ይከፈታል።የመክፈቻ ቀኑ በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወ/2/ፋ/ጽ/ቤት 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ይከፈታል።
14. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም
15. ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ጦር ሀይሎች ወደ 18 በሚወስደው መንገድ ሆላንድ ኢምባሲ ፊት ለፊት አባ ጅፋር መስጂድ አጠገብ ል/ክ/ከተማ ወረዳ 2 አስ. ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ስልክ ቁጥር 011-3-69-21-41
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት