Addis Zemen (Aug 22, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ፀሐይ ግባት ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የት/ዘመን ለት/ቤቱ ሥራ የሚያስፈልጉ ከዘህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
1. ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፡፡
2. የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ያለው፡፡
3. የግብር ክሪላንስ ያለው፡፡
4. የአቅራቢነት ሊስት መመዝገባቸውን በዌብ ሳይት ማረጋገጥ የሚችል፡፡
5. VAT መመዝገባቸውን መረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ የጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራች የጥቃቅን የአምራችነት ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
7.ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ የሚችል፡፡
- ሎት 1 የደንብ ልብስ ሲፒኦ ብር 4,000.00 / አራት ሺ ብር ብቻ/ (2%)
- ሎት 2 የስፌት ዋጋ ሲፒኦ ብር 1500.00 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ/ 2%
- ሎት 3 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች / የፅሕፈት መሣሪያ ሲፒኦ ብር 10000.00 /አስር ሺህ ብር ብቻ/ (2%)
- ሎት 4 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ሲፒኦ 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ (2%)
- ሎት 5 ህትመት ሲፒኦ 4000.00/ አራት ሺ ብር ብቻ/ (2%)
- ሎት 6 የሕክምና ዕቃዎች ሲፒኦ ብር 3000.00 /ሶስት ሺህ ብቻ/ (2%)
- ሎት 7 የፅዳት ዕቃዎች ሲፒኦ ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር ብቻ/(%)
- ሎት 8 ልዩ ልዩ መሣሪያዎች /ዕቃዎች ሲፒኦ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር ብቻ (2%)
- ሎት 9 የማሽነሪ መሣሪያዎች ዕድሳት ሲፒኦ ብር /3000.00 /ሦስት ሺ ብር ብቻ/ (2%)
- ሎት 10 ልዩ ልዩ ጥገናዎች ሲፒኦ ብር 5000.00 /አምስት ሺ ብር ብቻ/ (2%)
- ሎት 11 ቋሚ ዕቃዎች ሲፒኦ ብር /25000.00/ ሃያ አምስት ሺህ ብር ብቻ (2%)
- ሎት 12 ኤች ቨ ሲፒኦ ብር 2000.00 / ሁለት ሺህ ብር ብቻ (2%)
- ሎት 13 ተገጣጣሚ የቢሮ ዕቃዎች ሲፒኦ / 1000.00 / አንድ ሺህ ብር ብቻ/(2%)
- ሎት 14 የግብርና እቃ ሲፒኦ /500.00/ አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ/ (2%) * ጠቅላላ ድምር 80,000 /ሰማንያ ሺ ብር ብቻ/
8. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 06 እየቀረቡ መግዛት ይችላል፡፡
9. ተጫራች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በመምጣት ዋጋ የሞላችሁበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
10. ጨረታው በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ታሽጎ በ5፡00 /አምስት ሰዓት/ ይከፈታል፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
11. ተጫራቾች ያሸነፉበት ዋና ውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
12 ተጫራቾች ጨረታውን ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና የሚቀርብባቸው እቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሸን (Specification)መሠረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
13. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበት እቃ በራሱ ትራንስፖርት መሥሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
14. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነሰም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡–በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ፀሐይ ግባት ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት፡፡
፤– ከአማኑኤል ቶታል ጀርባ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡– 0112 736 397
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ወረዳ 3 የፀሐይ ግባት ቅድመ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት