Addis Zemen (Aug 22, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ ትዕግስት በቀለ እና የፍ/ባለዕዳ እነ አልጋነሽ ዘለቀ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጋሞ ዞን የጬንቻ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/18933 በ25/10/2016 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/113218 ሐምሌ 25 ቀን 2017ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ከ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 407 በሴሪያል ቁጥር 008420 የካርታ ቁጥር አከ-08/2711/3407/ኤ.ካርታ በተመኔ ቱንጋ እና የዘለቀ ተካ ወራሾች ስም የተመዘገበ የቦታ ስፋቱ በሰነድ 45.94 ካ/ሜ ጠቅላላ በፕሮፖርሽ የሚደርሰው 53.94ካ/ሜ የሆነ በአካባቢው የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2.ካ/ሜ ይነካዋል አዋሳኞቹ በስተሰሜን ቤት ቁጥር 410 በስተደቡብ መንገድ/ባዶ ቦታ በስተምዕራብ መንገድ/ ባዶ ቦታ በስተምስራቅ ቤት ቁጥር 408 የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,675,494.44 (ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ አራት መቶ ዘጠና አራት ብር ከ44/100) ሆኖ የትራክሸን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት