የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት የተለያዩ የሳኒተሪ እቃዎች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት የተለያዩ የሳኒተሪ እቃዎች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 22, 2026)

የተለያዩ የሳኒተሪ እቃዎች ግዥ ግልጽ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር ////////////31/2018

ድርጅታችን የተለያዩ የሳኒተሪ እቃዎች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም

1. በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤

የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል በኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት C.R.D.A አጠገብ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታች ላይ ያልተመሰረተ 90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantes) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥር ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በአሥራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 430 በግዥ ዳይሬክቶሬት ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

4. ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት ከሲ.አር.. አጠገብ

ስልክ ቁጥር 0911 060 918 / 0920 276 648

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *