የዕድገት በስራ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የዕድገት በስራ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Lessan (Aug 22, 2026)

በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የእድገት በስራ ቅድመ መጀመረያና የመጀ/ደ/ት/ቤት
የግልፅ ጨረታ ቁጥር 01/2018 ዓ.ም

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1 የደንብ ልብስና የስራ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ 4000 ብር፡፡
  • ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 2000 ብር በመከፈል፡፡
  • ሎት 3. ለህትመት ስራዎች- የጨረታ ማስከበሪያ 500 ብር በመክፈል፡፡
  • ሎት 4. ልዩ ልዩ የህክምና እቃዎች  የጨረታ ማስከበሪያ 500 ብር በመክፈል።
  • ሎት 5. አላቂ የትምርት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 2000 ብር በመክፈል፡፡
  • ሎት 6. ልዩ ልዩ የፅዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 3500 ብር በመክፈል፡፡
  • ሎት 7. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች መግዣዎች  የጨረታ ማስከበሪያ 500 ብር በመክፈል።፡
  • ሎት 8. ለፕላንት እና ማሽነሪ እድሳት ጥገና  የጨረታ ማስከበሪያ 500 ብር በመክፈል፡፡
  • ሎት 9. ለፕላንት እና ማሽነሪ መግዣ- የጨረታ ማስከበሪያ 2000 ብር በመክፈል
  • ሎት 10. ለህንፃ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች መግዣ  የጨረታ ማስከበሪያ 2000 ብር በመክፍል፡፡

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በልደታ ክ/ከተማ እድገት በስራ የመጀ/ደ/ት/ቤት በመቅረብ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መዉሰድ ይቻላል፡፡

2. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉ የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግስት ግ/ን/አስ/ ኤጀንሲ ድህረ ገፅ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የቲን እና የቫት ተመዘጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዶቹ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችሃል፡፡

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ዉስጥ በሚገኘዉ የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) የስራ ቀናት ዉስጥ ልደታ ክ/ከተማ እድገት በስራ የመጀ/ደ/ት/ቤት የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማሰገባት አለባችሁ፡፡

5. ለጨረታ ከቀረቡ እቃዎች ዝርዝር ዉስጥ ት/ቤቱ እስከ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ፡፡

6. የጨረታዉ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ንብረት በራሱ ትራንስፖርት እድገት በስራ ት/ቤት ማቅረብ ይኖረበታል፡፡

7. ጨረታዉ በአድስ ልሳን ጋዜጣ በወጣ 10ኛዉ ቀን 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታዉ ሳጥን በማግስቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በት/ቤቱ አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻና መዝጊያ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡

8.ተጫራቾች ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይኖርባቸዋል (ከሎት 1 እስከ ሎት 10 ድረስ)

9.ት/ቤቱ (መስሪያ ቤቱ) የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ፡፡

10. የዘገየ ጨረታና በመክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለዉም፡፡ ዋጋ ሲሞሉ ቫትን አካተዉ ይሙሉ (ያቅርቡ)፡፡

አድራሻ፡- ልደታ ክ/ከተማ እድገት በስራ የመጀ/ደ/ት/ቤት ተክለ ሀይማኖት በርበሬ በረንዳ ሞሀ ለስላሳ ፊት ለፊት ስልክ፡- 0115-157 055

በአ/አ ከ/አስተዳደር ት/ቢሮ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ ቤት የዕድገት በስራ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ
ት/ቤት