Addis Zemen (Aug 28, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የአብዲ ጃርሶ ት /ቤት ለ2019 ዓ.ም ለት/ቤት የሰራተኞች የካፌ አገልግሎት አወዳደሮ ለማስራት ይፈልጋል፡፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያማሉ ተወዳደሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1/ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ የገቢዎች ባለስልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃቸውንና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀትና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2/ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በተጨማሪም ካሽ ሪጅስተር ማሽን/ ደረሰኝ ያላቸው
3/ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለአስር/10/ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 እብዲ ጃርሶ ፋይናንስ ት/ቤት ዘወትር /2:30-11:30/ በስራ ሰዓት ሰነዱን 300 ብር መግዛት ይችላሉ፡፡
4/ ዋጋ በምታቀርቡበት ጊዜ ቫትን ያካተተ/ TOT/ መሆን አለበት።
5/ ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በለሚ ኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 06 አብዲ ጃርሶ ፋይናንስ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲሆን ጨረታው ከወጣበት በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን የሚከፈት ይሆናል።
6/ ተጫራቾች ያሸነፉበት ማንኛውንም የመስተንግዶ አገልግሎት ማቅረብ /መስጠት/ ይኖርባቸዋል።
7/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር /10,000/ አሥር ሺህ ብር/በባንክ የተመሰከረለት የከፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው። የማወዳደሪያ እቃውን ከቫት ጋር ደምረው ይላኩልን፡፡
8/ ካፌው በት/ቤቱ በተዘጋጀ ቦታ የሚሰጥ ይኖርባቸዋል፡፡
9/ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– ለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 እብዲ ጃርሶ ፋይናንስ ት/ቤት ልዩ ስሙ ቦሌ አራብሳ ጃርሶ ገባ ብሎ።
የአብዲ ጃርሶ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትቤት
የአብዲ ጃርሶ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትቤት