የካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ፋ/ጽ/ቤት በስሩ ላሉት የተለያዩ ሴክተር ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ፋ/ጽ/ቤት በስሩ ላሉት የተለያዩ ሴክተር ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 29, 2026)

የአንደኛ ዙር ጨረታ ማስታወቂያ

የካ /ከተማ ወረዳ 07 //ቤት በስሩ ላሉት የተለያዩ ሴክተር /ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽሕፈት መሣሪያ፣

  • የፅዳት እቃዎች
  • የአይቲ ዕቃዎች፣
  • የአትክልት መሣሪያዎች፣
  • የኪራይ ኣገልግሎት፣
  • የፕሪንተር ቀለም፣
  • ደንብ ልብስ፣
  • የመኪና ዕቃ እና የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች ማቅረብ የሚገባቸው።

1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ

2. ግብር መለያ ቲን ነምበር ያላቸው

3. የታደሰ ንግድ ፍቃድና በተጨማሪም የንግድ ዘርፉን የሚገልጽ ማቅረብ የሚችሉ

4. የጨረታውን ሰነድ የካ /ከተማ ወረዳ 07 ፋይናንስ /ቤት ቢሮ ቁጥር 11 በግንባር በመምጣት የማይመለስ 800 /ስምንት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል።

5. ጨረታው ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናሉንና ኮፒውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6.ጨረታው በወጣበት በአስራ አንደኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ፋይናንስ /ቤት 400 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7.ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ የካ /ከተማ ወረዳ 07 //ቤት ይሆናል፡፡

8. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለባቸው  በዚህ መሰረት ሎት 1 11,708.00 ሎት 2 26,190,00 ሎት 3 27,781.00 ሎት 4 1,200.00 ሎት 7 17,260.00 ሎት 8 11,411.00 ሎት 9 6,440.00 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

9.ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዕቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለጽ በታሸገ ኤንቨሎፕ ያቅራቢ ማህተም እና በዋጋ ማቅረቢያው ዝርዝር ላይ ዝርዝሩን የሞላው ኃላፊ በእያንዳንዱ ዋጋ በተሞላበት ሰነድ ላይ በየገጹ በመፈረም ለዚህ ተብሎ የተዘጋጀውን የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሑፍ የሚገለጽላቸው ሲሆን ለጨረታው አፈጻጸም ውል ማስከበሪያ ለአሸነፈበት ጠቅላላ እቃ ዋጋ 10 ፐርሰንት ሲፒኦ በማስያዝ ውል የመዋዋል ግዴታ አለባቸው፡፡

11.ተጫራቾች የጽሕፈት መሣሪያ፣ ፅዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የፕሪንተር ቀለም እና የአትክልት መሣሪያዎች ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

12.ተቋሙ ካዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ውጪ ዋጋ መሙላት ተቀባይነት የለውም፡፡

13.በጥቃቅን የተደራጁ ተጫራቾች ካደራጃቸው አካል ኦርጂናል የድጋፍና አምራች መሆናቸው የሚገልጽ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡

14.ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ጊዜ 60 ቀናቶች ይሆናል፡፡

15.መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ አድራሻ የካ /ከተማ ወረዳ 07 ሲግናል ካምፕ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር፦ 0116-68 63 85

የካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት