በሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክ/ከ የሲዳ አዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለሰክቴር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃዎች፣ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ቋሚ ዕቃዎች) እና የደንብ ልብሶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክ/ከ የሲዳ አዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለሰክቴር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃዎች፣ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ቋሚ ዕቃዎች) እና የደንብ ልብሶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 01, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክ/ከ የሲዳ አዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለሰክቴር መ/ቤቶች አገልግሎት የምውሉ የተለያዩ:-

  •  የጽሕፈት መሳሪያ እና
  •  የጽዳት ዕቃዎች
  • ፈርኒቸር
  • ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ቋሚ ዕቃዎች)
  • የደንብ ልብሶች አወዳድሮ ለማግዛት

ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ/መረጃ በማቅረብ/ ተጫራቾች በጨረታው እንድሳተፉ ይጋብዛል::

  1. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ) ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታተይ የሥራ ቀናት ድረስ በሲዳ አዋሽ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::
  2. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምስክር ወረቀት ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ የሚያቀርቡ።
  3. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ያላቸው ፡፡
  4.  ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ለአንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በሲዳ አዋሽ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከሲዳ አዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ::
  5. በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ(ተዘግቶ) ልክ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሲዳ አዋሽ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ይከፈታል::ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል:: ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አይግደውም::
  6.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  7. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል::
  8. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርቦው ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያው ለመንግስት ገቢ ይሆናል::
  9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተገለፀው መሰረት የተመረተበትን ዕቃ ናሙና/sample/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል::
  10. ጥራት /Quality/ በሌላቸው እቃዎች ላይ (በኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች ከተሰጠ መስፈርት(standard) በታች የሚያቀርብ ተጫራች) መስሪያ ቤቱ የማይደራደር መሆኑን በቅድሚያ እናሳውቃለን::
  11. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትንማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታው ትቻለሁ ማለት አይችልም::
  12. ጽ/ቤታችን የሚያጫረታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው እስከ (20%)በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል::
  13. የመወዳደሪያ በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል::
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  15. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0935205127/0941340508/0912047566 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ::

የመንግስት ፋይናንስ ህግ እና መመሪያን የሚጥስ ማንኛውም ነገር ተቀባይነት የለውም::

አድራሻ፡- በሸገር ከተማ ገላን ክ/ከ ሲዳ አዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

በሸገር ከተማ ገላን ክ/ከ የሲዳ አዋሽ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት