በአራዳ ክፍለ ከተማ የደጃ/በላይ ዘለቀ ቁ1 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የእስቴሽነሪ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ለትምህርት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች፣ የቋሚ ዕቃ ለመግዛት፣ የጽዳትና ጥበቃ የደንብ ልብስና የመምህራን ጋውን ስፌት ለማሰፋት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአራዳ ክፍለ ከተማ የደጃ/በላይ ዘለቀ ቁ1 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የእስቴሽነሪ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ለትምህርት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች፣ የቋሚ ዕቃ ለመግዛት፣ የጽዳትና ጥበቃ የደንብ ልብስና የመምህራን ጋውን ስፌት ለማሰፋት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 01, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም

በአራዳ ክፍለ ከተማ የደጃ /በላይ ዘለቀ ቁı ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019 ዓ/ም የሚሆኑ

  • የእስቴሽነሪ እቃዎች፣
  • የጽዳት እቃዎች ፣
  • ለትምህርት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች፣
  • የቋሚ ዕቃ ለመግዛት፣
  • የጽዳትና ጥበቃ 
  • የደንብ ልብስና የመምህራን ጋውን ስፌት ለማሰፋት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

  1. በሙያው ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  2. በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክርነት ወረቀት የሚያቀርቡ።
  3. በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዚህን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በፋይናንስ ቢሮ መውስድ ይቸላሉ።
  5. በተጠየቁበት ዕቃ ናሙና ያላቀረቡ ነጋዴዎች ጨረታቸው ውድቅ ይሆናል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ከጠቅላላው ዋጋ 2% በት/ቤቱ ስም ሲ.ፒ.ኦ በማሲያዝ ከመወዳደሪያ ሰነድ ጋር
  7. ጋር በይናንስ ክፍል ቢሮ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡።
  8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የሚያቀርቡትንዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋና እና ኮፒ በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  9. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል።
  10. ት/ቤቱ የተለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት እና ሰራተኛ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
  12. ተጫራቾች አሸንፈው ውል በሚፈጽሙ ጊዜ ያሸነፋበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።

አድራሻ፡- ከየካቲት 12 ሆስፒታል ጀርባ ከናዝሪት ት/ቤት ከፍ ብሎ

በስልክ ቁጥር፡- 011-173-0598 እና 011-156-5246 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ አራዳ ክ/ከተማ

በ ወረዳ 06 ት/ጽ/ቤት የደጃ/በቀ ቁ.1 2ኛ ደረጃ ት/ቤት