Addis Zemen (Aug 31, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ግልፅ ጨረታ ቁጥI 006/2019 ዓ.ም
በአራዳ ክ/ከተማ የኢትዮጵያ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በመንግስት መደበኛ በጀት በተገኘ ገንዘብ በቂ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የትምህርት እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ልዩ ልዩ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ ልዩ ልዩ ቋሚ እቃዎች፣ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
1. በሙያው ዘርፍ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ዋና ምዝገባ ቲን፤ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉ መሆን አለበት።
2. በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
3. የተጨማሪ እሰት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዚህን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
4. ተጫራቾች የዘመኑን ግበር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀንጀምሮ ከቢሮ ቁጥር 37 መዉሰድ ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10000.00 (አስር ሺ ብር ብቻ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በት/ቤቱ ስም በተዘጋጀ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ስፒኦ ኦርጅናል ፖስታ ዉስጥ ከሰነዳቸዉ ጋር ማሸግ ይጠበቅባቸዋ። ተጫራቾችየሚያቀርቡትን የእቃ ዓይነት ናሙና ከጨረታዉ መከፈቻ ቀን በፊት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚያቀርቡትን ዋጋ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት የግዥዉን አይነት በኤንቨሎፕ ላይ በመጥቀስና ማህተም በማድረግ ት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 37 በተዘጋጀው ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸው።::
9. የጨረታ ሳጥን በ11ኛዉ የስራ ቀን 3፡00 ተዘግቶ በእለቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 37 ይከፈታል።
10. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት
11. የጨረታ አሸናፊው ተጫራች ዉል ከመዋዋሉ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ 10% ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለበት።
12. አሸናፊ ተጫራች የተገዙትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ተቋሙ ድረስ በማቅረብ ግቢ ማድረግ አለበት።
ማሳሰቢያ ት/ቤቱ በጨረታ ሰነድ ዉስጥ የተጠቀሱትን እቃወች ካለዉ በጀትና (የተሻለ መንገድ ካገኘ) እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የእቃዉን 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ፤ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፦ እንቁላል ፋብሪካ ሩፋኤል በሚወስደዉ መንገድ በስተቀኝ 100ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ 0934153534 0963810812
በአራዳ ክ/ከተማ የኢትየጵያ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት