Addis Zemen (Sep 01, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
በአዲስ አበባ አስተዳደር በጉለሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 ውስጥ የሚገኘው የአዲስ ዘመን አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለት/ቤቱ አገልግሎትየሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
- አላቂ የትምህርት መርጃ መሳሪያ
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- አላቂ የፅዳት እቃዎች
- የደንብ ልብስ
- የህክምና እቃዎች
- ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
- ለፕላን ማሽነሪ መሳሪያ መግዣ
- ህትመት
- የደንብ ልብስ ስፌት
- ለኮምፒተር እና ለፕሪንተር ቋሚ እቃዎች እድሳት እና ጥገና እና
- የሻይ ቡና ክበብ አገልግሎት
- የህንፃ እድሳት እና ጥገና መስጠት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በጨረታው እዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ሽሮ ሜዳ በእንጦጦ ማርያም መንገድ ሥላሴ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ላቭሊ አካዳሚ ጎን ባለው ቀጭን መንገድ 200ሜትር ገባ ብሎ ከሚገኘው አዲስ ዘመን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት ከላይ ለተጠቀሱት ዕቃዎች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ፋይናንስ ቢሮ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 200 /ሁለትመቶ ብር /በመክፈል መውሰድ ይቻላል።
2. ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ በእቃ ወይም አገልግሎት አቅራቢነት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ዊቭ ሳይት ድህረ ገፅ የተመዘገበ የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሊራንስ ማስረጃ መወዳደሪያ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
3. በጨረታው ለመካፈል በቅድሚያ ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ፤ ለአላቂ የቢሮ እቃዎች- 20000 ብር ፤አላቂ ትምህርት መርጃ እቃዎች 2000 ብር አላቂ የፅዳት እቃዎች 32000 ብር ልዩልዩ መሳሪያዎች 400ብር፡ ደንብ ልብስ ብር 40907 ብር፡ለሰራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት 2000 ብር፤ ህትመት 2200ብር ፤ የህምና እቃዎች 1560 ብር፣ኮምፒተር እና ለፕሪንተር እድሳት እና ጥገና 600 ለህንፃ ጥገና እና እድሳት 600 ፤ ለፕላን ማሽነሪ መሳሪያ መግዣ (ቋሚ እቃዎች ) 8000 ብር የሻይ ክቡብ አገልግሎት ለመስጠት 27804 ብር ነው፡፡ በእያንዳዱ ሎት በሲፒዮ ማስያዝ ይኖርበታል ጥቃቅን እና አነስተኛ አምራች ወይም ተጨማሪ እሴት ካልጨመረ እደማንኛውም ተጫረች ሲፒዮ ማስያዝ ይጠበቅባቹዋል።
4. ት/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ የእቃውን ብዛት ከውል በፊት 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው።
5. ተጫራቾች አሸናፊ የሆነበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት እና ሰራተኛ ገዥው ግምጃ ቤት ድረስ የማቅረብና የማውረድ እንዲሁም አስፈትሾ የማስረከብ ግዴታ አለበት።
6. ተጫራጮች ለሚወዳደሩበት እቃዎች አልባሳትና የትምህርት እቃዎች ናሙና ከጨረታው መክፈቻ ቀደም ብሎ ማቅረብ ይጠበቅባቹሀል ።
7. የጨረታ ሰነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
8. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩትን ዋጋ ፖስታ በማድረግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በስራ ሰዓት በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ፋይናንስ ቢሮ ቀን በ4፡30 ይከፈታል
10. ከጠቅላላ የዕቃው ዋጋ 10%ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
11. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ከቫት ጋር መሆን ይኖርበታል፡፡ቫት ሳያካትት ዋጋ ያስገባ ተጫራች እንደ ተካተተ ተደርጎ ይወሰድበታል።
12. ማሳሰቢያ መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሽሮሜዳ በእንጦጦ ማርያም መንገድ ሥላሴ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ዋን ላቭ አካዳሚ ጎን ባለው ቀጭን መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ ስልክ 0118124262 በመደወል ማግኘት ይቻላል
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክፍለ ከተማ የአዲስ ዘመን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት