በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የቦሌ ህብረተሰብ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የቦሌ ህብረተሰብ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 01, 2026)

አንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ የእቃ ግዢ ማስታወቂያ

የግዢ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የቦሌ ህብረተሰብ ቅድመ 1ኛ ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው ፣

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

5. ተጫራቶች ከዘህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸው ፡፡

ሎት ቁጥር የሎት ዝርዝር የተጠየቀው የጨረታ ማስከበርያ የኢትዮጵያ ብር

  • ሎት 1  የደንብ ልብስ  ብር 40,000
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች ብር 32,000
  • ሎት 3 አላቂ የትምህርት እቃዎች ብር 40,000
  • ሎት 4 የህትመት ስራዎች ብር 8,000
  • ሎት 5 የፅዳት እቃዎች ብር 24,000
  • ሎት 6. ቋሚ የቢሮ እቃዎች ብር 40,000
  • ሎት 7. ህንፃና ቁሳቁስ ጥገና እቃዎች ብር 40,000
  • ሎት 8 ፕላንትና ማሽነሪ እቃዎች ብር 61,000
  • ሎት 9. አላቂ የህክምና እቃዎች ብር 2,000

6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 04 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ 04 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ።

8. ጨረታው በ11ኛው ቀን በእለቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበርያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡

10.ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ናሙና ለማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ አለባቸው ::

11. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት የቦሌ ህብረተሰብ ቅድመ 1ኛ ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

12.ት/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ከቦሌ ድልድይ 400 ሜትር ገባ ብሎ ቦሌ ሆምስ ፊት ለፊት

ስልክ፡- 011 8 21 77 36

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 13 የቦሌ ህብረተሰብ ቅድመ 1ኛ፣ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት