በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የቦሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ ቋሚ የቢሮ መገልገያዎች፣ የደንብና የሌሊት ልብሶች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች/Furniture’s/፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የመኪና ጎማና ባትሪ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ለአንድ የበጀት ዓመት የሚያቀርብ አቅራቢ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የቦሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ ቋሚ የቢሮ መገልገያዎች፣ የደንብና የሌሊት ልብሶች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች/Furniture’s/፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የመኪና ጎማና ባትሪ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ለአንድ የበጀት ዓመት የሚያቀርብ አቅራቢ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 31, 2026)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የቦሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ አላቂ ቋሚ የቢሮ መገልገያዎች ፤የደንብና የሌሊት ልብሶች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች/Furniture’s/፤ የጽዳት ዕቃዎች እና የመኪና ጎማና ባትሪ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ለአንድ የበጀት ዓመት የሚያቀርብ አቅራቢ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው : መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

መስፈርቶች

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

2 ተጫራቾች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት ለምን ለምን ዓይነት ዕቃ እንደሆነ በሰነዶቻቸው ላይ በትክክል ለይተው መጻፍ አለባቸው።

3. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋለ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውን ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።

4. ተጫራቾች ከሙስናና ከማጭበርበር ተግባር ነጻ ስለመሆናቸውና የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ህግ ለማክበራቸው ከጨረታው ሰነድ ጋር ተያይዞ ያለውን ቅጽ መፈረም አለባቸው።

5. ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙናዎች ላይ በግልጽ በሚታይ የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ እቃ ላይ በማሳረፍ ማቅረብ አለበት።

6. ጨረታውን ለማደናቀፍ የሞከረ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ሆኖ

7. ለወደፊትም በመንግስት ግዥ ጨረታ ውስጥ የማይወዳደር ሲሆን ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል ፡፡ የሚቀርቡት ዕቃዎች በቀረበው ናሙናና ትዕዛዝ መሠረት ጥራታቸውን ጠብቀው ካልቀረቡና ማንኛውም ዓይነት ስህተት ቢፈጸም ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው ፡፡

8. እንዲያቀርቡ የሚታዘዙትን ዕቃዎች ድርጅቱ በራሱ ትራንስፖርት የመ/ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ አጓጉዞ ማስረከብ አለበት ፡፡

9. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ከመስሪያ ቤቱ ጋር በገባው ውል መሰረት ለ2019 የበጀት ዓመት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

10. የጨረታው አሸናፊ በግልጽ ማስታወቂያ ወይም በጽሁፍ ደብዳቤ ከተገለጸለት ዕለት አንስቶ በ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለአሸነፈባቸው ዕቃዎች ዋጋ 10% የጨረታ ውል ማስከበሪያ በኢንሹራንስ ጋራንቲ የተመሰከረ ቼክ/ Check / ወይም ጥሬ ገንዘብ አስይዞ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት ፡፡ ይህንን ባይፈጽሙ መ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ያደርጋል ፡፡

11. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ወክሎ ውሉን የሚፈርም የድርጅቱ ባለቤት ሳይሆን ተወካይ ከሆነ ህጋዊ ውክልና ኦሪጅናል እና የማይመለስ ኮፒ ይዞ መቅረብ አለበት ፡፡

12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 ሦስት መቶ ብር ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት በመክፈል ሰነዱን ከግዥ ክፍላችን ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ ፡፡

13. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለጨረታው ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት በቦሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በባንክ የተመሰከረለት ቼክ CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ ከጨረታው ኦርጂናል ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡

14. አሸናፊው እንደታወቀ ለተሸናፊዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ይመለሳል፡፡

15. ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በሚቀርቡ ናሙናዎች ላይ የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ እቃ ላይ በመምታት ማቅረብ አለበት፡፡

16. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ቆይቶ የሚጠናቀቅ ይሆናል ፡፡

17. ጨረታው ቆይቶ በ16ኛው ከቀኑ በ3፡30 ላይ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ በቦሬ ወረዳ አስተዳደር ግቢ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

18. የጨረታው የመግባቢያ ቋንቋ አማርኛ እና ኦሮሚኛ (አፋን ኦሮሞ) ነው ፡፡

19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው ።

ለተጨማሪ መረጃ ፡-በስልክ ቁጥር 046 6 67 02 61 ፣
046 6 67 00 23 ወይም 046 6 67 01 37 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የቦሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት