Addis Zemen (Aug 31, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መስተዳድር በሰሜን ሸዋ ዞን የአለልቱ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚ፣ አላቂ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፤ ህትመት እና የጽህፈት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተለዉን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
1. እቃዎቹን በጥራት ለማቀረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉና የንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱ ለዚህም ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
2 ለጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር / ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም” በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቀረብ የሚችል።
3. በግልም ሆነ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቀረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር / በመክፈል አለልቱ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ለ10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ5/1/2019 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ስዓት ተዘግቶ በዛዉ እለት ከቀኑ 8፡00 (ስምንት ሰዓት) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታዉ ይከፈታል።
7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፦ ተጫራቾች እቃዎቹን ጥራታቸውን የጠበቁ ሆነው በተባለው ጊዜና ቦታ ውስጥ አጠናቀው ማቀረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ
በስልክ ቁጥር 011631027/ 0924783034 /0913947513/0941070332 አለልቱ ወረዳ ፍርድ ቤት መጠየቀ ይችላሉ፡፡
አድራሻ — በደሴ/ደ/ብርሃን መንገድ በዋናዉ አስፋልት ከአ/ አ 55 ኪ.ሜ ከዋናው አስፓልት በስተግራ 100 ሜትር ገባ ብሎ ነዉ።
በሰሜን ሸዋ ዞን የአለልቱ ወረዳ ፍርድ ቤት