Addis Zemen (Aug 31, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2019 የበጀት አመት ለገላን ከከተማ ለማዘጋጃ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪዎች እና መኪኖች አወዳድሮ ማስጠገን ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ /መረጃዎች በማቅረብ/ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፍ ይጋብዛል፡፡
1- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
2- አቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
3- ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin/ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
4- የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
5- ከትራንስፖርት ቢሮ የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ(ሰርተፊኬት) እና ደረጃ 2(ሁለት)ፍቃድ ያለው መረጃ ማቅረብ የሚችል
6- መስሪያ ቤቱ በሚፈልግበት ቦታ (መኪና ወይም ማሽነሪዎቹ ተበላሽቶ የቆሙበት ቦታ)ሄዶ መጠገን ወይም መስራት የሚችል
7- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15 ተከታታይ የስራ ቀናት እና በስራ ሰዓት ለያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 1500.00 (አንድ ሺ አምስት መቶ ብር) በአካውንት ቁጥር 1064934721214 በማስገባት በገላን ክ/ከተማ ገቢዎች ባለስልጣ ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ ፡፡
8- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት ( 15) ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ በገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡
9- ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ (ተዘግቶ ልክ በዚሁ ቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
10- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000 (አምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
11- ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
12- ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል ፡፡
13- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ ቦኋላ በጨረታው ሰነድ ለይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይችልም፡፡
14- የመወዳደሪያ በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል ፡፡
15- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
16- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 4 45 01 82 (09-23 57 49 41) በመደወል እና በአካል ተገኝቶ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት/ገላን
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት