Addis Zemen (Sep 01, 2026)
ብሔራዊ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
በደቡብ ምዕ/ኢት/ሕ/ክልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ላሉት ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ የተለያዩ እቃዎችን ማለትም፡-
- ሎት 01 የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 02 የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 03 የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 04 የእንስሳት መድኃኒት ግዢ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ተጫራቾች ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. የተጨማ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2. ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ ተጫራቾች ለሎት 1. የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር፣ ለሎት 2. የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 250/ሁለት መቶ ሃምሳ ብር፣ ለሎት 3. የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 350 ሦስት መቶ ሃምሳ ብር/ እና ለሎት 4 የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ እየከፈሉ ከሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ላይ ዘወትር በሥራ ሠዓት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታውን መወዳደሪያ የእያንዳንዱን ዕቃ ነጠላ ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ለእያንዳንዱ ሰነድ ቢያንስ ሁለት ሁለት ኮፒ አድርገው በካፋ ዞን ሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. እያንዳንዱ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በየሎቱ ሲሆን ከስራ ፍቃዳቸውና ከተዛማጅ ፍቃድ ውጭ መወዳደር የተከለከለ ነው።
6. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለሎት 1 ብር 65000 /ስልሳ አምስት ሺህ ብር/ ፣ ለሎት 2 ብር 30000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ለሎት 3 ብር 50000/ሃምሳ ሺህ ብር /ብቻ እና ለሎት 4 ብር 40000 /አርባ ሺህ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ CPO የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው።
7. የጨረታ ፖስታ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በተመሳሳይ ዕለት ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን የመክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
9. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ እስከ ወረዳው ርዕሰ ከተማ ላይ ባለው የወረዳው ፋይ/ጽ/ቤት ድረስ በመገኘት ውል በመግባት ውል ከገባበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ በውሉ መሠረት ዕቃዎችን በወረዳው ፋይ/ጽ/ቤት ሺ ሺንዳ ከተማ ድረስ በማቅረብ ቆጥሮ ማስረከብ መቻል ይኖርበታል።
10. ከሎት 1-3 ለወጣው ጨረታ የዕቃ ናሙና ያለማቅረብ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ያደርጋል።
11. ከሎት 1-3 ለወጣው ጨረታ ተጫራቾች የዕቃ ናሙናውን ከጨረታ ፖስታው ጋር እስከ ወረዳው ፋይ/ጽ/ቤት ድረስ በማቅረብ የጨረታ ፖስታ ተከፍቶ የጨረታው አሸናፊ ሲታወቅ ጨረታን ያላሸነፈ ወዲያው ተመላሽ ተደርጐለት የሚወስድ ሆኖ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያመጣውን ናሙና በአደራ አስቀምጦ መሄድ መቻል ይኖርበታል።
12. አሸናፊው ድርጅት ያቀረበው እቃ ጥራቱንና መጠኑ የተጓደለ ከሆነ በራሱ ኪሳራ መቀየር የሚችል መሆን ይኖርበታል።
13. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው (CPO) ለተሸናፊው ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን አሸናፊ ድርጅት ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ እስከ 5ኛው ቀን ድረስ የውል ማስከበሪያ አስይዞ ውሉን የማይፈጽም ከሆነ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
14. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። ማሳሰቢያ፡-መ/ቤቱ የተሻስ አማራጭ ካገገ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡-በስልክ ቁጥር 047 668 0200/0431
በመደወል መረዳት ይቻላል።
የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት