Addis Zemen (Sep 01, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን፣ የጎላ ኦዳ ወረዳ የፋይናንስ ጽሕፈት ቤት በ2019 በጀት ዓመት የጎላ ኦዳ ወረዳ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በቀን 4/2/2018 ለጠየቀው የሕንጻ ግንባታ ፕሮጀክት በተመደበው በጀት መሠረት፣ መስፈርቱን የሚያሟሉና የደረጃ 5 (GC/BC Grade 5) እና ከዚያ በላይ የሕንጻ ግንባታ ፈቃድ ያላቸውን ተቋራጮች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ብቁ የሆናችሁ ተጫራቾች በሙሉ በጨረታው እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።
|
የፕሮጀክቱ ባለቤት |
የፕሮጀክቱ ስም
|
የስራ ቦታ
|
የፕሮጀክቱ ዓይነት
|
ብዛት
|
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)
|
የፕሮጀክቱ ጊዜ
|
|
የጎላ ኦዳ ወረዳ አስተዳደር
|
መሶብ [የአንድ ማዕከል አገልግሎት]
|
ጎላ ኦዳ ወረዳ፣ ቡርቃ ከተማ
|
የጂ+2 (G+2) ሕንጻ ግንባታ
|
1
|
100,000
|
|
ለውድድር የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፦
1. ከፌዴራል ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የደረጃ 5 (GC/BC Grade 5) እና ከዚያ በላይ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት፣ ከሕጋዊ የፌዴራል እና የኦሮሚያ ክልል አካላት የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) እና ለ2019 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2. የመንግሥትን የግብር ግዴታ ስለመወጣታቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡ።
4. በፒፒኤ (PPA/EGP) የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ።
5. የኮንትራክተር የብቃት/ፈቃድ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
6. በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) መጠን መቶ ሺህ ብር (100,000.00) በጎላ ኦዳ ወረዳ የፋይናንስ ጽሕፈት ቤት ስም ማቅረብ አለባቸው።
7. ከዚህ ቀደም ሥራዎችን ወስደው ቢያንስ 90 በመቶ ያጠናቀቁ ተቋራጮች ከቀጣሪው አካል የስራ አፈጻጸም ወይም ነጻ የመሆኛ (clearance) ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች የማይመለስ 5,000 (አምስት ሺህ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን፣ በጎላ ኦዳ ወረዳ የፋይናንስ ጽሕፈት ቤት የግዢ ክፍል በመገኘት መግዛት ይችላሉ።
9. የስርዝ ድልዝ ወይም የተፋቀ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
10. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 (ሃያ አንድ) የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ እስከ 21ኛ የስራ ቀን ድረስ ቆይቶ በ 22ኛው የስራ ቀን ይዘጋል፡፡
11. ጨረታው በ 21/1/19 ቀን በ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ፣ በዚሁ ቀን በ 4፡30 ሰዓት በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በጎላ ኦዳ ወረዳ የፋይናንስ ጽሕፈት ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
12. ተጫራቾች የቴክኒክና የፋይናንስ የጨረታ ሰነዶቻቸውን ለየብቻ ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪም አንድ ዋና (Original)፣ አንደኛ ኮፒ (1st Copy) እና ሁለተኛ ኮፒ (2nd Copy) ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ፣ በድርጅቱ ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ ማህተም እና ፊርማ በግልጽ ተለይቶ መቅረብ አለበት።
13.ተጫራቾች ለዚህ ውድድር በጽሕፈት ቤቱ የተዘጋጁትን የጨረታ ቅጾች መሙላት ይኖርባቸዋል፤ በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ገጽ ላይ የድርጅትዎ ስም፣ የዓቃቤ ሕግ/ የወኪል ስም፣ ፊርማ እና ማህተም መረጋገጥ አለበት። ያልተረጋገጠ ወይም ያልተሟላ ሰነድ ማቅረብ ከውድድር ውጪ የሚያደርግ ሲሆን፣ በዚህ ምክንያት ለሚመጣው ማንኛውም ችግር ተጫራቹ ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡
14.ሰነዱን የገዛ ማንኛውም ተቋራጭ በፕሮጀክቱ ቦታ ላይ በመገኘት የቦታ ምልከታ (site visit) ማድረግ አለበት። ስለዚህ ማንኛውም ተቋራጭ ወይም ወኪል በማህተም እና በፊርማ የተረጋገጠ የቦታ ምልከታ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርበታል። የቦታ ምልከታ ምስክር ወረቀት ሳይቀርብ የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት እንደሌላቸው ተጫራቾች አስቀድመው ሊያውቁት ይገባል፡፡
15. የፋይናንስ ጽሕፈት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. በአጠቃላይ ለሕንጻ ተቋራጮች በግዢ መመሪያው ላይ የተቀመጡት መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ ይሆናሉ።
17. ለተጨማሪ መረጃ በሥራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0934308357 / 0915140701/0963911703 መደወል ይችላሉ።
የጎላ ኦዳ ወረዳ አስተዳደር ፅህፈት ቤት