የተስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የተስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 01, 2026)

የ2019 ዓ.ም ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የተስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በመጀመሪያ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሎት ቁጥር

የእቃው አይነት

ሲፒኦ/C.P.O

ሎት 1

አላቂ የቢሮ እቃዎች 6212

11,812.00

ሎት 2

አላቂ የፅዳት እቃዎች 6218

9,000.00

ሎት 3

የደንብ ልብስ ግዥ 6211

11,200.00

ሎት 4

አላቂ የትምህርት እቃዎች 6215

8,500.00

ሎት 5

ለሚኒስትሪሚኒግ 6419

910.00

ሎት 6

ልዩ ልዩ የእጅ መሳሪያዎችና የሕንፃ መሳሪያዎች 6219

975.00

ሎት 7

ለቋሚ እቃዎች ግዥ 6314

5,430.00

ሎት 8

ለፕላንት ለማሽነሪና ግዥ 6313

6,000.00

ሎት 9

ለፕላንት ለማሽነሪና ለመሳሪያ የእድሳት ጥገና 6243

650.00

ሎት 10

የክሊኒክ እቃዎች 6214

7,250.00

ሎት 11

ኬሚስትሪ LAB እቃዎች 6215

1,000.00

ሎት 12

አላቂ የትምህርት ዕቃዎች 6215

5000.00

ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. የአገር ውስጥ ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. የአገር ውስጥ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሪላንስ/ማስረጃ ማቅረብ የሚትችሉ፡፡

3. የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ቲን ነምበር ፤ ቫት ተመዝገቢ እና የo8 ዓም በጀት አመት የታደሰ የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው::

4. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

5. ሎት 1፤2፤3፤4፤5፤6፤7፤8፤10፤ 11 እና 12 የሚወዳደሩ ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የእቃውን ናሙና ንበረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው የብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ከሆኑ ከአደራጃቸው አካል በዘርፉ መደራጀታቸውን የሚገልጽና በጨረታ ስራ ላይ መሳተፍ እናደሚችሉ የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚጫረቱበትን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በመቅርብ መግዛት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ያጠቃለለ እና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልቶ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በተስፋ ብርሀን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት 10 የስራ ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ11ኛ ቀን 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አዳራሽ ቁጥር 9 ይከፈታል፡፡

10. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸው እቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የማስያዝና የግዢ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡

11. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ከሆኑ ካደራጃቸው አካል መደራጀታቸውን የጨረታ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

12. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ ከጨረታው ያሰርዛል፡፡

13. መ/ቤቱ ጠቅላላ ለጨረታው ካቀረበው ብዛት 20% ከፍና ዝቅ ብሎ የግዢ ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡

14. ለጨረታው የተሰጠው ዋጋ ለ6ዐ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡

15. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ሾላ ገበያ ፊት ለፊት ከንግድ ባንክ ዝቅ ብሎ

ለስተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-658-80-08 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የተስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት