Addis Zemen (Sep 02, 2026)
የግልጽ የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 05 አዲስ ራዕይ ቅድመ መደ እና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ጨረታውን ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
|
ሎት ቁጥር |
የሎት ዝርዝር |
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ/ በኢትዮጵያ ብር |
|
ሎት-1 |
የደንብ ልብስ |
ብር 6,000 |
|
ሎት-2 |
አላቂ የቢሮ ዕቃዎች |
ብር 4,000 |
|
ሎት-3 |
አላቂ የትምህርት ዕቃዎች |
ብር 6,000 |
|
ሎት-4 |
አላቂ የፅዳት ዕቃዎች |
ብር 5,000 |
|
ሎት-5 |
ልዩ ልዩ መሣሪያዎች |
ብር 2,000 |
|
ሎት-6 |
ለፕላንት፣ ማሽነሪ መሣሪያዎች |
ብር 5,000 |
|
ሎት-7 |
ለሕንፃ፣ የሕንፃ ቁሳቁስና ተገጣጣሚ |
ብር 4,000 |
6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 2 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቢሮ ቁጥር 2 በመምጣት ዋጋው የሚሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ በየሎቱ የተዘጋጀውን የዋጋውን CPO በማካተት ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8. ጨረታው በአስረኛው (በ10ኛው) ቀን 10፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ልክ ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ዕቃዎች መሥሪያቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ አለባቸው።
10. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሽነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ለትምህርት ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
11. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
12. ት/ቤቱ ለጨረታው ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% ድረስ የመቀነስም ሆነ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- መገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ ኮከብ ሕንፃ አለፍ ብሎ 24 ሕንፃ አጠገብ ወይም ጀርባ
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 893 2560
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የአዲስ ራዕይ የመጀ/ደ/ት/ቤት