Addis Zemen (Sep 02, 2026)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ
ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
በድጋሚ የወጣ የደንብ ልብስ የሚሰፋ ብትን ጨርቆች፣ ካኪ ቴትረን 6000፣ ካኪ ጨርቅ፣ የተዘጋጀ የሴትና የወንድ ሸሚዞች፣ የወንድና የሴት ጫማዎች የዝናብ ልብስ፣ ዣንጥላ፣ ግዥ ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ሰነድ ቁጥር 009/2018፦-
ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር በድጋሚ የወጣ የደንብ ልብስ የሚሰፋ ብትን ጨርቅ ካኪ ቴትረን 6000፣ ካኪ ጨርቅ፣ የተዘጋጁ የወንድና የሴት ሸሚዞች፣ የወንድና የሴት ጫማዎች፣ የዝናብ ልብስ፣ ዥንጥላ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ እየገለጽን፡-
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የፈሉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ህጋዊ አካል የተፃፈ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ምዝገባ ሰርተፍኬት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት በሚገኘው መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤከርስቲያን ፊት ለፊት ፊንፊኔ ህንፃ 7ኛው ፎቅ ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ፋይናንስ ግዥ ንብረት አስተዳደር መምሪያ መግዛት ይችላሉ።
4. ማንኛውም ተጫራች ብር 50000.00 (ሀምሣ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ /CPO/ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርቸዋል።
5. አሽናፊው ድርጅት በአምስት ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት መፈረም አለበት።
6. የጨረታ መዝጊያው ሰዓት ከደረሰ እና የጨረታ ሣጥነ ከታሸገ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
8. ጨረታው አአ መስቀል አደባይ ፊንፊኔ ህንፃ ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ፋይ/ሃገር ንብ/አስ/መምሪያ 7ኛ ፎቅ የሚከፈት ይሆናል።
9. ለጨረታ በሚመጡበት ወቅት ሳምኘል ናሙና እና ዋጋውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ የውል ማስከበሪያ የአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ከድርጅቱ ጋር ውል በመግባት ወደ ስራው ይገባል።
11. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
12 የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ላይ ቀኑ የሥራ ቀን ከሆነ በዕለቱ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በዋናው መ/ቤት አዲስ አበባ ይከፈታል።
13. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:-
- ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፡- መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ፊንፊኔ ህንፃ 7ኛ ፎቅ
- ስልክ ቁፕር 011 552 1009/ 011 552 1458/ ፖ.ሣ.ቁ. 9515 ፋክስ 011 551 3654 አ/አበባ
ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር