ብርሃን ባንክ አ.ማ. መኖሪያ ቤት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ብርሃን ባንክ አ.ማ. መኖሪያ ቤት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Sep 06, 2026)

የሐራጅ ማስታወቂያ

ብርሃን ባንክ አማ ከባለእዳዎቹ ላይ ለሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረትቶች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል::

  1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን የ1/4 (አንድ አራተኛ) (ሲፒኦ) በብርሃን ባንክ አ.ማ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ::
  2.  የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን እንዳሸነፈ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ አለበት:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል::   በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች  ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል::
  3. የመኖሪያ፣ ንግድ እና መጋዘን ቤቶቹ ጨረታ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ይከናወናል::
  4.  የጨረታ አሸናፊው በሚገዛው ንብረት ላይ የሚፈለግ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያዎች እና የሊዝ ክፍያዎች ይመለከተዋል::
  5. መያዣ ሰጪዎች ሐራጁ በሚከናወንበት ቦታ ቀንና ሰዓት መገኘት ይችላሉ:: ባይገኙ ግን ሐራጁ በሌለበት ይካሄዳል::
  6. በባንኩ ብድር መምሪያ መስፈርት መሰረት እና በተሰጠው ጊዜ ውስጥ የሚፈለግበትን ለሚያሟላ ተጫራች ባንኩ በከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል::
  7. ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጐብኘት ይቻላል::
  8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው

የመኖሪያ ቤት

ተ.ቁ

የተበዳሪዉ ስም

የመያዣ ሰስም

መኖሪያ/ የንግድ ቤት የማገኝበት አድራሻ

በቦታው ስፋ በካሬ ሜትር

 

የንብረቱ አገልግሎት

 

የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

 

የጨረታ መነሻ ዋጋ

 

ጨረታዉ የሚካሂድበት ቀን እና ሰዓት

1

ታምሒንካ

ታምሒንካ

ሻሸመኔ ከተማ ደ/ቦቃ ቀበሌ

140 ካ.ሜ

 

መኖሪያ ቤት

 

11980

 

2,350,000.00

 

መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡30

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 011-6506900 እና 011-6506276 በመደወል መጠየቅ ይቻላል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *