በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የመ/ሜዳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በመ/ሜዳ ከተማ ለሚያሰራው Phase One (Lot-1) የG+3 ህንፃ ግንባታ እና (lot 2) የG+0 Service office Building/ ህንፃ ግንባታ ስራ የማቴሪያል አቅርቦት ከእነ ፊኒሽንግ ማቴሪያል እና አገልግሎት ግዥን ጨምሮ ግንባታውን ለሚገነባ ህንፃ ተቋራጭ ለማስገንባት ህጋዊ የግንባታ ስራ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የመ/ሜዳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በመ/ሜዳ ከተማ ለሚያሰራው Phase One (Lot-1) የG+3 ህንፃ ግንባታ እና (lot 2) የG+0 Service office Building/ ህንፃ ግንባታ ስራ የማቴሪያል አቅርቦት ከእነ ፊኒሽንግ ማቴሪያል እና አገልግሎት ግዥን ጨምሮ ግንባታውን ለሚገነባ ህንፃ ተቋራጭ ለማስገንባት ህጋዊ የግንባታ ስራ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 08, 2026)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታው አይነት የግንባታ ጨረታ ቁጥር 1/2018

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የመ/ሜዳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በመ/ሜዳ ከተማ ለሚያሰራው Phase One (Lot-1) G+3 ህንፃ ግንባታ እና (lot 2) G+0 Service office Building/ ህንፃ ግንባታ ስራ የማቴሪያል አቅርቦት ከእነ ፊኒሽንግ ማቴሪያል እና አገልግሎት ግዥን ጨምሮ ግንባታውን ለሚገነባ ህንፃ ተቋራጭ ለማስገንባት ህጋዊ የግንባታ ስራ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከደረጃ 5 እና በላይ በግንባታ ስራ ተቋራጭ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላችሁ ተጫራቾች ከተቁ1-14 የተዘረዘሩትን ለጨረታው የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በመ/ሜዳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቀርባችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

  • ሎት 1 Phase One (Lot_1) G+1 Building ህንፃ ግንባታ
  • ሎት 2 (Lot-2) G+0 Service office Building ህንፃ ግንባታ

ስለዚህ ጨረታውን ለመጫረት ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሠረት ቀርባችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ተጫራቾች በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሰውን ከሎት 1 እስከ ሎት 2 ያሉትን የህንፃ ግንባታ ስራዎችን ለመጫረት በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያበቃ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።

3. የግዥ መጠን ብር 500,000.00 እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. የግንባታ ስራ ዝርዝር (Bill Of Quantities) ከጨረታ ስነዱ ማግኘት ይቻላል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 2,000 /ሁለት ሺህ ብር / በመክፈል በቢሮ ቁጥር 2 የገቢ/ግዥ//ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተመሰከረ ቼክ CPO በማሰራት አቅራቢው ለመጫረት የሚፈልገውን የግዥ ሎት ዓይነት የጠቅላላ ዋጋውን ብር 250,000 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ ክጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት።

8. ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን አሟልተው ኦርጅናልና ኮፒ ዶክመንቶችን የቴክኒካል እና የፋይናንሺያል ፖስታውን በመለየት በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት በተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 230 እስከ 1130 ሰዓት ባለው የስራ ሰዓት የገቢ ግዥ// ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት

9. በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

10. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 400 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከጠዋቱ 430 በሮ ቁጥር 2 የገቢ ግዥፋ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

11. የጨረታ አሸናፊው እንደተገለፀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ (CPO) ለተሸናፊዎች 20 ቀን በኋላ ይመለሳል።

12. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ በተገለፀ 5 ቀን ውስጥ አስፈላጊውን 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ወዲያውኑ ወደ ስራ ክፍሉ መጥቶ ውል መፈፀም አለበት፡፡ ይህን ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል

13. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

14. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0116851335/0116850770/0909322641 ላይ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላል።

የመሐል ሜዳ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *