Addis Zemen (Sep 08, 2026)
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አአህስኮ/ብግጨ/ዕግ/001/2019
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረት ስራ ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የሚገዛው እቃ (አገልግሎት) አይነት |
የሎት ምድብ |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
|
1 |
የተለያዩ አላቂ የቢሮ እቃዎችና የጽ/መሳሪያዎች |
ሎት አንድ |
30,000 |
|
2 |
የአይቲ ዕቃዎች |
ሎት ሁለት |
50,000 |
|
3 |
የፅዳት ዕቃዎች |
ሎት ሦስት |
30,000 |
|
4 |
የሰራተኞች ደንብ ልብስ |
ሎት አራት |
5,000 |
|
5 |
የተለያዩ የህትመት ውጤቶች |
ሎት አምስት |
30,000 |
|
6 |
የተሽከርካሪ ጌጣጌጥ ዕቃዎች |
ሎት ስድስት |
30,000 |
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡–
በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT 15%)፣ የታክስ ክሊራንስ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ድርጅቶችን አንዲወዳደሩ እየጋበዘ የተጫራቾች መወዳደሪያ መስፈርትና ሁኔታዎችን እንደሚከተለው ቀርበዋል፡–
- ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10 (አስር) በመቶ ሲ.ፒ.ኦ በማቅረብ በ15 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈፀም የሚችል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመያዝ በኮሚሽኑ ፋይናንስ በመክፈል በግዥ ንብረት አስ/ጠቅ/አገል/ዳይሬክቶሬት ቢሮ 3ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለጸው የብር መጠን መሰረት ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነዶች ጋር በሲፒኦ ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ዋስትና (Addis Ababa City Administration Cooperative commission) በማለት አሰርተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ፣ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ብሎ በመለየት ለየብቻው በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ሕጋዊ ማኅተምና ፊርማ በማድረግ በኮሚሽኑ በግዥ ንብረት አስ/ጠቅ/አገ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ 3ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለ ቀን ጀምሮ 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት ሕዝባዊ ወይም ኃይማኖታዊ በዓል ከሆነ ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ሌላ ማስታወቂያ ማውጣት ሳያስፈልግ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይከፈታል፣
- ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ
መስከረም ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው ቴሌ ጋራጅ አካባቢ ከሚገኘው ካሮጋ ፋርማ ህንፃ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011 126 36 93
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረት ስራ ኮሚሽን