የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሎጅና ሪዞርቶች (ጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ∶ ሃላላ ኬላ ኢኮ ሎጅና ወንጪ ኢጃ ኢኮ ሎጅ) የሚሆኑ የመንገድ ዳር ምልክቶችን (supply and installation of lodge and resort roadside traffic signage) የሚያቀርቡና የሚተክሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሥራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሎጅና ሪዞርቶች (ጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ∶ ሃላላ ኬላ ኢኮ ሎጅና ወንጪ ኢጃ ኢኮ ሎጅ) የሚሆኑ የመንገድ ዳር ምልክቶችን (supply and installation of lodge and resort roadside traffic signage) የሚያቀርቡና የሚተክሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሥራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 09, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: GGP-T641

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሎጅና ሪዞርቶች (ጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ ሃላላ ኬላ ኢኮ ሎጅና ወንጪ ኢጃ ኢኮ ሎጅ) የሚሆኑ የመንገድ ዳር ምልክቶችን (supply and installation of lodge and resort roadside traffic signage) የሚያቀርቡና የሚተክሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሥራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡

1. ለሥራው ብቁ የሆኑና የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት/TIN/ ያላቸው እና በመንግሥት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፍቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር GGP-T641 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 400,000.00 /አራት መቶ ሺህ ብር/ በባንከ በተረጋገጠ .. (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቋም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንከ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡

4. ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ 150 ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡ አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።

5. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረታ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በተለያየ ኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ግዥ ከፍል እስከ መስከረም 28, 2019 . 830 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ግዥ ከፍል

ግሩፕ ጀነራል ፕርቼዝ

ስልክ ቁጥር፡ +251-115-17-46-56/8655

ሜይል፡ EmiruG@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *