Addis Zemen (Sep 09, 2026)
ሁለተኛ ዙር የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለጤና ቢሮ እና ለተጠሪ ተቋማት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን በመጋበዝ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤
- ሎት 1 የፅዳት ዕቃ እና የሴቶች የግል ንፅህና መጠበቂያ
- ሎት 2 ፍራሽ አንሶላ ትራስ እና ትራስ ጨርቅ
- ሎት 3 በተመረጡ አጠቃላይ (Comprehensive HP) የጤና ኬላዎች የሶላር ኃይል ሥርዓቶች አቅርቦት፣ተከላ እና ሥራ ማስጀመር፣
- ሎት 4 በተመረጡ መሠረታዊ (Basic HP) የጤና ኬላዎች የሶላር ኃይል ሥርዓቶች አቅርቦት፣ተከላ እና ሥራ ማስጀመር፣
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል የምትችል
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል የምትችል
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል የምትችል
- የግብር ከፋይ መለያ ምስክር ወረቀት TIT Number/ ማቅረብ የሚችል የምትችል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ/AT ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል የምትችል መሆን ይኖርባቸዋል
- ለሎት 3 እና 4 ብቻ በተጨማሪ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- በኤሌክትሪካል፣ በኤሌክትሮሜካኒካል፣ በታዳሽ ኃይል ሥርዓቶች፣ በሶላር ኃይል ተከላ፣ በኤሌክትሪክ ሥራዎች ወይም በተመሳሳይ የሥራ መስኮች የተሰማራ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤
- የደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የኤሌክትሮሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ፈቃድ፤
- የታደሰ የታክስ ክሊራንስ (ከዕዳ ነጻ) ማረጋገጫ ሰርተፍኬት፤
- በሶላር ኃይል ሥርዓቶች አቅርቦትና ተከላ ላይ የተሳካ የሥራ ልምድ የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ፤
- ለሶላር PV ሞጁሎች፣ ኢንቨርተሮች፣ ባትሪዎች እና ቻርጅ ኮንትሮለሮች ከአምራቹ
- የተሰጠ የውክልና ደብዳቤ (Manufacturer’s Authorization Letter) ወይም የተፈቀደለት አከፋፋይ መሆን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት፤
- ተመሳሳይ የሶላር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮጀክቶችን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቅን የሚያሳይ ማስረጃ።
በመሆኑም ተጫራቾች ሰነድ በእያንዳንዱ ሎት መግዥ የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ቀርበው በመከፍል ዘወትር በመንግስት ሥራ ሰዓት 15/አስራ አምስት/ ቀናት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ግዥ ክፍያ ንብረት አሰር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ሎት 1 የፅዳት ዕቃ እና የሴቶች ግል ንፅህን መጠበቂያ 100,000/ አንድ መቶ ሺህ ብር /ብቻ
- ሎት 2 ፍራሽ፣ አንሶላ፣ ትራስ እና ትራስ ጨርቅ 100,000 ብር/ አንድ መቶ ሺህ ብር/ ብቻ
- ሎት 3 እና 4 ለጤና ኬላዎች ሶላር አቅርቦት፣ተከላ እና ሥራ ማስጀመር የ200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ስም CPO/የባንክ ጋራንት/ በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመጻፍ በሰመ/በሙጫ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ግዥ ክፍያ ንብ/ አስ/ር ዳይሬክቶሬት በማቅረብ ለዚህ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ 1 /አንድ/ ኦሪጂናል እና 2/ሁለት/ ኮፒ ፖስታዎች ለየብቻቸው በሰም/በሙጫ/ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
ተጫረቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፤አድራሻ፤ ማህተምና ፊርማቸውን በግልጽ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ 5፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ይከፈታል። የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
አሸናፊው ድርጅት በተወዳደረበት ቦታ ንብረቱን የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር– +2514734508
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ