Reporter (Sep 09, 2026)
የተለያዩ የIT እቃዎች ድጋሚ የወጣ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ HBSCITEQUIPMENT/01/0001/26
የተለያዩ የIT እቃዎች ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክስዮን ማህበር የተለያዩ የIT እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በማመልከቻ ሲጠይቁ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦
1. ሕጋዊ ምዝገባ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያደሱ ሆነው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፣
3. በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳደሪዎች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው፤
4. ተጫራቾች ከላይ የተገለፁት መስፈርት አሟልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 29ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በአካዉንት ቁጥር 1000004335299 በመክፈል የገባበትን ስሊፕ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፤
5. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ
ሀ) ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸውን በታሸገ የጨረታ ማስከበሪያ 150,000 /አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ሌሎች ተቀባይነት ያላቸው የጨረታ ማስከበሪያዎች ከኦርጅናል ዶክመንት ጋር በማድረግ በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሽግ /ቴክኒካል በሚል በመለየት፤
ለ) ለፋይናንሺያል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ በማሽግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ /ፋይናንሻል በሚል በመለየት እስከ 29ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
6. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በሐበሻ ቢራ አ.ማ ስም እና ከቴክኒካል ዶክመንት ኦሪጅናል አብሮ መቅረብ አለበት።
7. ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱት መስፈርቶች ሙሉ ለሙሉ ያላሟላ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል
8. የጨረታው ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ምንረከበው ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ30ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።