Addis Zemen (Sep 10, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ፍሬህይወት አንዳርጋቸው እና በፍ/ባለዕዳ እነ ከተማ ትሳሱ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/209765 በ15/03/2018ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/212955 በ07/05/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር አዲስ በመስክ ልኬት የተገኘ የቦታ ስፋቱ 99.04 ካ/ሜ የሆነ ሰነድ አልባ ማህደር ያለው ይዞታው ቤቱ መብት ያልተፈጠረለት እና ካርታ ያልወጣለን ሰነድ አልባ ስለሆነ ከፍ/ባለዕዳ ወደ ገዥው ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሳይኖረው የስም ዝውውር አገልግሎት ለመስጠት የማይቻል ሲሆን ነገር ግን በአዲስ አበባ ከተማ መ/ል/አስ/ቢሮ በመብት ፈጠራ ቡድን በኩል መመሪያ እና አሰራር የሚፈቅደውን አሟልተው ከተገኙ ለገዥ መብት በመፍጠር በስሙ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተዘጋጅቶ የሚሰጠው ሲሆን አዋሳኞቹ በሰሜን የመሰረት ማሞ ቤት በደቡብ የእግር መንገድ በምስራቅ የጸዳለ አለሙ ቤት በምዕራብ የእግር መንገድ የሚያዋስኑት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,055,335.20 (ሶስት ሚሊዮን ሃምሳ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ አምስት ከ20/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት