የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለምርት ግብዓት የሚሆን ባህርዛፍ ግንድ በጉዶበረት ቀበሌ እና አባሞቴ ቀበሌ ባሉ ደን ሳይቶች ውስጥ ስለሚጭን ለሚጭኑት ገልባጭ መኪኖች መተላለፊያ የሚያገለግል በጫካው ውስጥ ለውስጥ ጊዜያዊ መንገድ በኤክስካቫተር ማሽን የጠረጋ ስራ ማሰራት እንዲችል በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ማሽኑን /400 ሰዓት/ በመከራየት ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለምርት ግብዓት የሚሆን ባህርዛፍ ግንድ በጉዶበረት ቀበሌ እና አባሞቴ ቀበሌ ባሉ ደን ሳይቶች ውስጥ ስለሚጭን ለሚጭኑት ገልባጭ መኪኖች መተላለፊያ የሚያገለግል በጫካው ውስጥ ለውስጥ ጊዜያዊ መንገድ በኤክስካቫተር ማሽን የጠረጋ ስራ ማሰራት እንዲችል በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ማሽኑን /400 ሰዓት/ በመከራየት ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 11, 2026)

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ /የተ/የግ/ማህበር ለምርት ግብዓት የሚሆን ባህርዛፍ ግንድ በጉዶበረት ቀበሌ እና አባሞቴ ቀበሌ ባሉ ደን ሳይቶች ውስጥ ስለሚጭን ለሚጭኑት ገልባጭ መኪኖች መተላለፊያ የሚያገለግል በጫካው ውስጥ ለውስጥ ጊዜያዊ መንገድ በኤክስካቫተር ማሽን የጠረጋ ስራ ማሰራት እንዲችል በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ማሽኑን /400 ሰዓት/ በመከራየት ማሰራት ይፈልጋል

በዚህ መሰረት፡

1. በዘርፉ የተሰማራና የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያለው

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር ያላቸው

3. የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 – 3 የተጠቀሱትና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 50,000.00 /ሃምሣ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው

6. ተከራይ ድርጅት ከደ/ብርሃን ከተማ ሥራው የሚሰራበት ጫካ ድረስ የማድረስ ኃላፊነት አለበት፣ ነገር ግን ስራው ሲጠናቀቅ የአከራይ ድርጅቱ በራሱ ወጪ ይመልሳል።

7. የአንዱ ሳይት ሥራ ሲጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ ሳይት ማሽኑ ሎቤድ የሚያስፈልገው ከሆነ ሎቤድ አቅርቦ የማዘዋወር ኃላፊነት የተከራይ ድርጅት ነው።

8. አሸናፊ ተጫራች በስራ ቦታ ላይ ከነዳጅ ወጪ በስተቀር የኤከስካቫተሩን የዘይት፣ ቅባት፣ ግሪስ፣ ሰርቪስ፣ ቀላልና ከባድ ጥገናዎች፣ የጎማ ጥገናና ግዢ፣ የሹፌር ደመወዝ እና አበል እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን በራሳቸው ይሸፍናሉ። እንዲሁም የራሱ ኦፕሬተር ሊኖረው ይገባል፡፡ የኦፕሬተር ሰርቪስ ተጫራቹ ማቅረብ አለበት።

9. ማሽኑ በስራ ላይ እያለ ቢበላሽ አሸናፊው ተጫራች በራሱ ወጪ የተበላሸውን የማስተካከል ስራ የሚሰራ ሲሆን በቀላሉ ማስተካከል የማይችል ከሆነ በራሱ ወጪ አንስቶ በምትኩ ሌላ ማሽን የማስገባት ግዴታ አለበት

10.ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው

11. በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፤ ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።

13. ጨረታው 16ኛው ቀን 400 ታሽጎ 430 ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም።

14.የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ላይ ወይም እሁድ ከዋለ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

15.አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 1% ያስይዛል።

16. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከካምፓኒው ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።

17. /ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 0910368437 ደውለው ይጠይቁ።

የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር

/ብርሃን

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *