Addis Zemen (Sep 12, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003/2010 ዓ.ም
ፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ኦሪጂናል የመኪና መለዋወጫ እቃዎች እና ሌሎች አገልግሎት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 ለአገር አቋራጭ ኦርጅናል አውቶቢስ መለዋወጫ ፤ በድጋሚ የወጣ
- ሎት 2 የከተማ አውቶቢስ ኦርጅናል መለዋወጫ፤ በድጋሚ የወጣ
- ሎት 3 ለውጭ ጥገና የተለያዩ ተሸከርከሪዎች ኦርጅናል መለዋወጫ፤ በድጋሚ የወጣ
- ሎት 4 ለልዩ የአገር አቋራጭ አውቶቢሶች ጎማ 315/80/R/22.5 20PB እና የከተማ አውቶቢሶች ጎማ 295/80/B/22.5 18 PR መግዛት ይፈልጋል፤ በድጋሚ የወጣ
- ሎት 5 የሰራተኛ ክበብ ኪራይ አገልግሎት፤ በድጋሚ የወጣ
- ሎት 6 ዲስክቶፕ ኮምፒውተር እና ፕሪንተር፣ በድጋሚ የወጣ
- ሎት 7 የሰራተኛ የዱቤ ህክምና አገልግሎት፤
- ሎት 8 የባስ ካፒቴን የጤና ምርመራ አገልግሎት፤
- ሎት 9 የድሬድዋ ማደያ ኪራይ አገልግሎት፤
- ሎት 10 የሸበሌ ቤቶች ኪራይ አገልግሎት፤
1. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር የስራ ቀናት ከሎት 1 እስከ ሎት 8 ለእያንዳንዱ ሎት 1000 በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በአካል በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
2. ከሎት1 እስከ ሎት 8 ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ ምዝገባና የታደሰ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የብቃት ማረጋገጫ እና የአቅራቢዎች የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆነ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) ያለቸው፤ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ከሎት 1 እስከ ሎት 8 ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የሚያቀርቡትን የጨረታ ሠነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሁለት ፖስታ በማዘጋጀትና በኢንቨሎፕ በማሸግ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ኃላፊነት በተሰጠው አካል ተፈርሞበት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 2% ሲፒኦ /Bid Bond/ ወይም በባንክ የተመሰከረለት በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች ለሎት1- 4 ለእያንዳንዱ ሳምፕል ማቅረብ አለበት።
6. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኃላ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል።
7. አገልግሎታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሜክሲኮ ወደ ልደታ
ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው ለተጨማሪ መረጃ፡-ስልክ ቁጥር 011-5-50-45-64
ፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት