Addis Zemen (Sep 13, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001
መልካ ዳንሴ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት አመት የተለያዩ ቋሚና አላቂ የቢሮና የትምህርት እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።
1.በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የታክስ ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና በዘመኑ ግብር መክፈላቸው ሕጋዊ ደረሰኝ ወይም የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
|
ሎት |
የአገልግሎት አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
ሎት 1 |
የጽሕፈት መሣሪያዎች እና አላቂ የቢሮ እቃዎች |
19,983 |
|
ሎት 2 |
የደንብ ልብስ |
54,000 |
|
ሎት 3 |
የፅዳት እቃዎች |
30,000 |
|
ሎት 4 |
የትምህርት እቃዎች |
10,000 |
|
ሎት 5 |
ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እና ቋሚ የቢሮ እቃዎች |
10,000 |
|
ሎት 6 |
ለማሽነሪ ጥገና |
44,000 |
2. ተጫራቾች ከዚህ በላይ በሰንጠረዥ በሚመለከተው መሰረት በሚወዳደሩበት ሎት ፊት ለፊት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ (cpo) በመልካ ዳንሴ የመ/ደ/ት/ ቤት ስም በማሠራት ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባችኋል።
3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመስስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በየሎቱ በመክፈል ከት/ቤቱ ፋይናንስ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 4 መልካ ዳንሴ የመ/ደ/ት/ቤት ግዢ ክፍል በመምጣት የጨረታውን ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱንም ሆነ የጨረታ ማስከበሪያ እንዲሁም የውል ማስከበሪያ በነጻ መስተናገድ የሚችሉ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ሁሉ የአምራችነት ድጋፍ ደብዳቤ ካደራጃቸው አካል ማምጣት የሚችሉት ማህበራቶች ብቻ ናቸው።
4. ትምህርት ቤቱ ያዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋውን ከነቫቱ ሞልቶ እና የድረጅቱን ሕጋዊ ማህተም አድረጎ ማቅረብ አለበት።
5. የጨረታ ሰነዱ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን በዓል ካልሆነ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ቀኑ በዓል ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተባለው ስዓት የሚከፈት ይሆናል።
6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የጨረታ ሰነድ በኤንቬሎፕ በማሸግ ዋና እና ኮፒ መሆኑን በግልጽ ለይቶ በመጻፍ ማስገባት ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ናሙና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት መቅረብ ያለበት ሲሆን ለአንድ እቃ ከአንድ በላይ ናሙና ማቅረብ አይቻልም።
7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ገዥ ፈፃሚው መልካ ዳንሰ ትምህርት ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. የዘገዩ ጨረታ እና በመክፈቻ ላይ ያልተነበበ እንዲሁም ግልጽ ያልሆነ ወይም የማይነበብ ጽሑፍ በጨረታ ተቀባይነት የለውም።
9. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን መሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍስ ከተማ ወረዳ 14 ከሰፈራ ዝቅ ብሎ ወይም ኃይሌ ማራቶን ፊት ለፊት ሰላም ገሮሰሪ ገባ ብሎ ሀና ፉሪ አዲሱ ኮንዶሚኒዬም አጠገብ
መልካ ዳንሴ የመ/ደ/ት/ቤት