Addis Zemen (Sep 14, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከ በወረዳ 10 ስር የሚገኘው የብርሃን በር ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከመንግሥት ከተመደበለት መደበኛ እና ውስጥ ገቢ በጀት ለ2019 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ አይነት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የደንብ ልብስ (የልብስ ስፌትን ያካትታል)
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3 አላቂ የትምህርት እቃዎች
- ሎት 4 ሌሎች አላቂ እቃዎች
- ሎት 5 ህትመት
- ሎት 6 የተለያዩ መፅሐፍት
- ሎት 7 ቋሚ እቃዎች ለመግዛት የሚፈልግ ሲሆን
የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
- ተጫራቾች የ2017 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መሊያ ቁጥር(TIN)የተሰጠው፤
- ወቅታዊ የ2017 ዓ.ም የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በጨረታው መሣተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ሊስት (SUPPLIER LIST) ውስጥ የተመዘገቡ፤
- በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ የጨረታ ተሳትፎ ከገቢዎችና ጉምሩክ ጽ/ቤት ቀኑ ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከብርሃን በር ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ ቤት ፋይናንስ ክፍል ከጧቱ 2፡30-11፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ሕጋዊ የድርጅት ማህተብና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የእቃዎች ዝርዝር ላይ የእያንዳንዱን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ሰነዱን አሸገው ዋናውን እና ኮፒውን ለያይተው ጨረታው እስከሚያበቃበት 10ኛው ቀን እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከዋለ ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም።የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት ይከፈታል ማንኛም ተጫራች መጫረት የሚችለው በሚመለከተው የንግድ ሥራ ፍቃድ (ሥራ ዘርፍ) ብቻ ነው።ከጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅታችሁ የዋስትና ደብዳቤ ለሚያመጡ ድርጅቶች በሚወዳደሩበት ዘርፍ የራሳችሁ ምርት አምራች) መሆናችሁን የሚገልፅ መረጃ በማቅረብ በአመረታችሁት እቃ ላይ ብቻ የምትወዳደሩ መሆኑን እናሳውቃለን። ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከታች ለተዘረዘሩት ሎቶች በተቋሙ ስም ሲፒኦ (CPO) በማሠራት ከዋናው ሰነድ ጋር ማያያዝ ይኖረባቸዋል።
|
ሎት 1 |
ሎት 2
|
ሎት 3
|
ሎት 4
|
ሎት 5
|
ሎት 6
|
ሎት 7
|
|
0.5% |
0.5%
|
0.5%
|
1%
|
2%
|
1%
|
1%
|
|
9000 |
6500 |
4500 |
20000 |
7000 |
1500 |
15000 |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የተጫረቱበትን እቃዎች ናሙና⁄ ሳምፕል ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ቫትን ጨምረው ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መሙላት አለባቸው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ውል ከመፈረማቸው በፊት የውል ማስከበሪያ የተጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።
- ብርሃን በር ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በጨረታው ከሚቀርቡት የእቃዎች ብዛት አሸናፊ ከሆነው ድርጅት እስከ 20% ድረስ መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
- ትምህት ቤቱ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፤
- ተጫራቾች ያስገቡትን ሳምፕል ጨረታው ከተጠናቀቀ በኋላ በጊዜው ካልወሰዱ ለሚደርሰው ጉዳት ተቋሙ ተጠያቂ አይሆንም።
- አድራሻ፡- አጠና ተራ ከተቃጠለው ሕንፃ ፊትለፊት ስልከ ቁጥር 011 273 9672/ 011 279 2458
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 10 ብርሃን በር ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት