Addis Zemen (Sep 13, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለግቢው ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ ከ60ሰው በላይ የመጫን አቅም ያለው ተሸከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ጨረታውን መሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሆስፒታሉ በሚገኘው የግዥ ሥራ አስፈጻሚ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ በ200 ብር በመክፈል በመውስድ የመወዳደሪያ ዋጋችሁን በመሙላት
- የታደሰ መንጃ ፈቃድ፣ የቲን ሰርተፊኬት፣ በዘመኑ የቴክኒክ ምርመራ የተደረገበትን ቦሎና የባለቤትነት መታወቂያ ሊብሬ _ ኮፒ፣ ለዘመኑ የታደሰ የመድን ዋስትና እንዲሁም ለሶስተኛ ወገን አስገዳጅ የመድን ዋስትና የገቡበትን ሰነድ ኮፒ አያይዛችሁ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30 6፡30 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ሥራ አስፈጻሚ ክፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 15000 ብር /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ CPO /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን በ08፡00 ተዘግቶ በ15ኛ ቀን ከሰዓት በኃላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመክፈቻውም ቀንቅዳሜና እሁድ ወይም በሕዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913213696 ደውሉ መጠየቅ ይችላሉ
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል