የደልጊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አላቂ የጽዳት ዕቃዎችንና የጽህፈት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የደልጊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አላቂ የጽዳት ዕቃዎችንና የጽህፈት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Sep 14, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የደልጊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አላቂ የጽዳት ዕቃዎችንና የጽህፈት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  •  ሎት.1 አላቂ የጽዳት ዕቃዎችን ፣
  • ሎት2. የጽህፈት መሳሪያ ፤

 ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ፡፡

2. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡

3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና እቃዉ ከብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሽ) ብር በላይ ከሆነ ቫት ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ወይም ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒዩ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሆስፒታሉ ህጋዊ ደረሰኝ ተቆርጦ ከሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡

7. የጨረታ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደልጊ ሆስፒታል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ04/01/2019 ዓ.ም እስከ 22/01/2019 ዓ.ም ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 3፡00 በሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ 3፡30 ላይ ሳጥኑ ይታሸጋል።

9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደልጊ ሆስፒታል ግዥ ፋይናስ ቢሮ በቀን 22/01/2019 ዓ.ም 4፡00 ላይ ይከፈታል ። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡

10. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) ደልጊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ድረስ መጥተዉ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

11. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ ያላስያዘና ውል ያልፈፀመ ከሆነ ግዥ ፈጻሚው አካል የጨረታውን ማስከበሪያ የመውረስ መብት ይኖረዋል።

12. ክፍያው የሚፈፀመው በውሉ መሰረት ይሆናል ።

13. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

14. የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡

15. በጨረታው ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በመመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡

16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደልጊ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ ።

17. አሸናፊው የሚለየዉ በሎት ወይም በዝቅተኛ ጥቅል ድምር ዉጤት ነዉ፡፡

የደልጊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *