የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቋሚና አላቂ እቃዎች፣ የደንብ ልብስና ጫማ፣ መጋረጃ፣ የፅዳት እቃዎች እና የመኪና ዕቃና ጎማ ከሀገር ውስጥ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቋሚና አላቂ እቃዎች፣ የደንብ ልብስና ጫማ፣ መጋረጃ፣ የፅዳት እቃዎች እና የመኪና ዕቃና ጎማ ከሀገር ውስጥ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 15, 2026)

የግልጽ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01 2019 ዓ.ም

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል እቃዎችን የ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ዙር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡

  • ቋሚና አላቂ እቃዎች፣
  • የደንብ ልብስና ጫማ፣
  • መጋረጃ፣
  • የፅዳት እቃዎች 
  • የመኪና ዕቃና ጎማ

ከሀገር ውስጥ ተጫራች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው ለመሳታፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች አሟልተው መገኛት ይኖርባቸዋል።

  1. በንግድ ዘርፍ ወይም በመስኩ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2. የመንግስት ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ወቅታዊ የሆነ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  4. የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  5. ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  6.  ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለጹ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ የኦርጅናሉን ይዘት በጠበቀ መልኩ በግልጽ የሚነበብ መሆን አለበት።
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 (አምስት ሺህ) ብር ሕጋዊ ከሆነ ባንክ የተረገጋጠ (CPO) በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ስም አሰርተው ከሚያቀርባቸው ሠነዶች ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው። ይህ አንዳላ ሆኖ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ አስቀድሞ ከባንክ ማረጋገጫ የሚወሰድ ይሆናል።
  8. ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 7 ላይ የተጠቀሰውን (CPO) ካላቀረበ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
  9. ለጥቃቅን ኢንተርፕረይዞች ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ፋንታ ከአደራጁ መ/ቤት የተጻፈ ወቅታዊ የሆነ ሕጋዊ የድጋፊ ደብዳቤ መቅረብ ይኖርበታል።
  10. ተጫራች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዶክመንት ወይም የጨረታው ሰነድ ከደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድቤት ወሊሶ ከተማ ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በአካል በመቅረብ የዕቃውን ምድብ አይነት /lot/ የማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር/ ይህ ማስታወቂያ በዚህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ05/01/2019 እስከ 25/01/2019 ዓ.ም መግዛት ይችላሉ።
  11. ጨረታውን ለማሰናከል የሚሞከር ተጫራች ከጨረታው ውጪ ሆኖ ወደፊት በሚደረገው በማንኛውም ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፤ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብም ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  12. የጨረታው ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ የሚቆይ ይሆናል።
  13. የጨረታው ሰነድ በ 26/01/2019 ከጠዋቱ እስከ 4:00 ድረስ ለጨረታ በተዘጋጀለት የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው የሚከፈተው በዚህ እለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።
  14. መስሪያ ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆና በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. ከላይ በተራ ቁጥር 1-14 ሳያሟላ የሚቀረብ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ

አድራሻ፡-የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ወሊሶ ከተማ

ስልክ ቁጥር፡- 0113411484/0113411396

Email: mmosk@oromiyaa.gov.et  ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ

የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት