የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት የተሽከርካሪ ዓመታዊ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት የተሽከርካሪ ዓመታዊ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 16, 2026)

በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

01/2019

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት የተሸከርካሪ ዓመታዊ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡

  1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባብነት ያለውና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ ዌይብ ሳይት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ከዌይብ ሳይት አትመው ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ የሚችሉ ወይም በክልሎች በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የግዥው መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ሥራ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ በቢሮው የተዘጋጀውንና የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 7 ቀርበው በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድና የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአግባቡ በማዘጋጀት በፖስታ አሽገው ጨረታው ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ቀን እስከ 11፡25 ሰዓት ድረስ በቢሮው ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት የመጨረሻው ቀን 11:30ሰዓት ላይ ተዘግቶ ቀጥሎ ባለው 11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ 10ኛው እና 11ኛው ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ላይ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ3፡00 ሰዓት ተዘግቶ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንዱስትሪ ልማት ቢሮ ስም ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. የፋይናንሻልና የቴክኒክ ሰነድና ሲ.ፒ.ኦ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው አየር ላይ መቆያ ጊዜ ከሚያበቃበት የመጨረሻው ቀን ጀምሮ ላሉት45 ተከታታይ ቀናት የሚያገለግል መሆን ይኖርበታል
  9. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት በ 05 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የጥገና አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በመያዝ በ 15 ቀናት ውስጥ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ጥገና ውል መግባት የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
  10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 046-221-9988 / 046-220-03-26 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

ሀዋሳ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *