ዲኬቲ ኢትዮጵያ ለድርጅቱ የቢሮ አገልግሎት የሚውል አንድ (01) አነስተኛ ኤስቪ (Small SUV) ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ዲኬቲ ኢትዮጵያ ለድርጅቱ የቢሮ አገልግሎት የሚውል አንድ (01) አነስተኛ ኤስቪ (Small SUV) ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Reporter (Sep 16, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ዲኬቲ ኢትዮጵያ (ድንቅ ክስተት ለጤና) የተባለ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ማህበራዊ ግብይትን በመትከል የቤተሰብ እቅድን ለማስፋፋት ኤችአይቪን ለመከላከል፣ እንዲሁም የእናቶችና ህፃናት ጤናን ለመጠበቅ የሚያስችሉ  ምርቶችን በማሰራጨት በሲቪል ማህበረሰብ ባለስልጣን ምዝገባ ቁጥር 0062 ተመዝግቦ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በኤቻይቪ እና የስነ ልቦና ተዋልዶ ጤና ላይ የራሱ አስተዋፃኦ በማድረግ ላይ ያለው የውጭ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ለድርጅቱ የቢሮ አገልግሎት የሚውል አንድ (01) አነስተኛ ኤስቪ (Small SUV) ተሸከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትት ይፈልጋል።

የተሸከርካሪው ዝርዝር መገለጫ (Vehicle Specification)

  • የተሸከርካሪው ዓይነት (Type) አነስተኛ ኤስ. (Small SUV)
  • ሞዴል (Model): Toyota RAV4 Hybrid
  • የምርት ዘመን (Model Year) 2025 ወይም ከዚያ በላይ (2025 and above)
  • የሞተር መጠን (Engine Capacity) 2.5L ወይም ከዚያ በላይ፣ 4 ሲሊንደር (2.5L or more 4 CYLINDER)
  • ማርሽ/ትራንስሚሽን (Transmission): CVT
  • የኤሌክትሪክ ሞተር አይነት (Electric Engine Type): Permanent Magnet Synchronous
  • የነዳጅ ዓይነት (Fuel System) ቤንዚን (Petrol
  • የዊልቤዝ መጠን (Wheelbase) 2690 ሚ.ሜ (2690mm)
  • የመቀመጫ ብዛት (Seating Capacity): 5 ሰው
  • ከመሬት ያለው ከፍታ (Ground Clearance): 200 ሚሜ (200 mm)
  • የጎማ ዓይነት (Wheels): አልሙኒየም /17 ኢንች (Aluminum/17 inch)
  • የደህንነት ኤርባን (Airbags): የጎን፤ የካርቱን፣ የሾፌር፣ የጎን ተሳፋሪ እና የሾፌር ጉልበት ኤርባን (Side, Curtain, Driver, Passenger, Driver Knee)
  • ዋስትና (Warranty): 3 ዓመት ወይም 100,000 . (3 years/ 100,000km)

የጨረታ ደንቦችና መመሪያዎች፡

1. ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው.

2. የመኪና ማስረከቢያ ቦታ፡ ከገርጂ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ከጉና መጋዘን ቀጥሎ በሚገኘው መጋቢ መንገድ ላይ ወጋገን ባንክ ገባ ብሉ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት።

3. ተጫራቾች መኪናውን የሚያስረክቡበትን ትክክለኛ ጊዜ (Delivery Period) በሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ (Quotation) ላይ በግልጽ ማመልከት አለባቸው።

4. የጨረታ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን፡ መስከረም 11/2019 ከሰዓት 11:00

5. የጨረታ መክፈቻ ቀንና ስዓት፡ መስከረም 12/2019 ከሰዓት 8:00

6. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተባለው ቀንና ሰዓት ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።

7. ድርጅቱ ማንኛውንም ጨረታ በሙሉ ወይም በከፊል ያለምንም ግዴታ የመቀበል ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው.

ስልክ ቁጥር፡ +251 911 317100 / +251 911 357228


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *